7ኛ ጠቅላላ ሃገራዊ ምርጫ፣ የህዝብ ተሳትፎና የዲሞክራሲ ግንባታ ጉዞ በኢትዮጵያ
ምርጫ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታዋን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ታሪካዊ ፋይዳ አለው ።
7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በሚሊዮን የሚቆጠሩ መራጮች ማልደው ተነስተው በየምርጫ ጣቢያዎቹ በመገኘት ቀጣይ እጣ ፈንታቸውን እና ሀገሪቱን ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት የሚመራውን መንግስት ለመምረጥ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።
7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለመምረጥ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ምዝገባ ማካሄዳቸው የሚታወስ ሲሆን የድምፅ መስጠት ሂደቱ ላይም ሕዝቡ ያሳየው ተሳትፎ እጅግ ከፍተኛ እና ታሪካዊ ነበር።
የዘንድሮው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሀገሪቱ የፖለቲካ እና የልማት ጉዞ ላይ ትልቅ ምዕራፍ የሚከፍት ሲሆን፥ ህዝቡ በነፃነትና በንቃት በመሳተፍ የዜግነት ድርሻውን ተወጥቷል።
በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተስተዋለው የመራጮች ሰልፍ ህዝቡ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ያለውን ጽኑ ፍላጎት ያሳየበት ሆኗል። በተለይም የሴቶች፣ የወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች የመጀመሪያ ጊዜ መራጮች ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑ ተስተውሏል።
ይህ ምርጫ ከፖለቲካዊ ውሳኔነቱ ባሻገር በሀገሪቱ የኢኮኖሚ መረጋጋት፣ በማህበራዊ ልማትና በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች ላይ ቀጣይነት ያለው እድገት ለማምጣት መሰረት የሚጥል ነው።
ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ማካሄዷ በራሷ፥ የዲሞክራሲ ጉዞዋ ወደ ኋላ የማይመለስ መሆኑንና በትክክለኛ መስመር ላይ እየተጓዘች ለመሆኗ ትልቅ ማረጋገጫ ነው።
#Prosperity