"በመስዋዕትነት የተገኘውን ስርዓት በመስዋዕትነት እንጠብቃለን" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች የህዝቡ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነዉ
ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት አስመልክቶ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ክፍለ ከተሞች በለውጡ ለተገኘው ድልና ስኬት እውቅና የሚሰጥ ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል።
ሰልፈኞቹ በመልዕክቶቻቸው ከመጋቢት እስከ መጋቢት የተመዘገቡ የስኬት ጉዞዎችን በመግለጽ፤ በመጋቢት 24 ተምሳሌታዊ ጉዞ እና መሰረታዊ ርምጃ የተመዘገቡ ስኬቶችን እያደነቁ ነው።
በለውጡ መንግሥት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ተግባራትን በመደገፍ፣ በቀጣይም የተሻለ ስራ እንዲሰራ ከመንግሥት ጋር በትብብር እንደሚሰሩ የሚያረጋግጡ መልዕክት እያስተላለፉ ይገኛል።