Prosperity Party

39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ዛሬ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ በህብረቱ ዋና መስሪያ ቤት በይፋ ይጀመራል። 

በታላቁ አህጉራዊ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች የዲፕሎማሲ ማዕከል ወደሆነችው አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን፤ ከተማዋም እንግዶቿን በክብር ተቀብላ አስተናግዳለች።

ይህ ጉባዔ አዲስ አበባ በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የማይተካ የዲፕሎማሲ ሚና ዳግም የሚያረጋግጥ ነው።
 
መሪዎቹ ለሁለት ቀናት በሚቆየው ስብሰባ አህጉራዊ ትብብርን በሚያጠናክሩ ወቅታዊና ስልታዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ።

ኢትዮጵያም በጉባዔው ብሔራዊ ጥቅሟን በሚያስጠብቁ እና አህጉራዊ ትስስርን በሚያጎለብቱ አጀንዳዎች ላይ በንቃት ለመሳተፍ ዝግጅቷን አጠናቃለች።

የዘንድሮው ጉባዔ “ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ቃል ነው የሚካሄደው።

ይህ አጀንዳ ለአፍሪካ ሁለንተናዊ እድገትና ለህዝቦቿ ጤና መሰረት የሆነ ቁልፍ ጉዳይ ሲሆን፤ መሪዎቹ በውሃ ደህንነትና በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ የሚያስተላልፏቸው ውሳኔዎች አህጉሪቱን ወደ ብልጽግና ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ባለፉት ሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የ48ኛው የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ለዛሬው የመሪዎች ጉባዔ ግብዓት የሚሆኑ ቁልፍ አጀንዳዎችን አዘጋጅቶ አጠናቋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party