Prosperity Party

"ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር የኢትዮጵያን እና የህዝቦቿን ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በትኩረት ይሰራል"- የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ፍቃዱ ተሰማ

ጥር 03 2018 ዓ.ም

"ጠንካራ አደረጃጀት፤ ለጠንካራ ፓርቲ" በሚል መሪ ቃል በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ሲካሄድ የነበረዉ የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ የ2018 የመጀመሪያ 6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተጠናቋል።

በመድረኩ ማጠናቀቂያ የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የፓርቲው ዋና ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር  አቶ ፍቃዱ ተሰማ እንደተናገሩት ያለፉት ስድስት ወራት ስራዎች የሚመሰክሩት ይህን ግዙፍ ፓርቲ የሚመጥን ጠንካራ አደረጃጀት ለመገንባት በሚያስችል ደረጃ አደረጃጀቶችን በመመርመር፣ በመፈተሽ እና መልሶ በማደራጀት ብቁ እንዲሆኑ ለማስቻል የተከናወኑ ተግባራት የሚበረታቱ እንደሆኑና ውደፊትም ተጠናክረዉ የሚቀጥሉ መሆናቸዉን ገልፀዋል።

የሚገጥሙንን ፈተናዎች በመደመር መንግስት እሳቤና እይታ ወደ ዕድል በመቀየር የኢትዮጵያንና የህዝቦቿን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራም አፅንኦት ሰጥተዋል።

በየደረጃው የሚታዩ ቁልፍ ችግሮችን በአግባቡ በመለየት አደረጃጀትን እንደ አንድ ራሱን የቻለ ግብ በማየትና በውጤት በመለካት በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት ዉስጥ የተመዘገቡ ዉጤቶችን በማላቅ፤ ዉስንነቶችን የቀጣይ 6 ወራት እቅድ አካል በማድረግ እና ወደ ጥንካሬ በመቀየር ጠንካራ አደረጃጀት መፍጠር እንደሚገባም አክለዉ ገልፀዋል።

የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት አባል እና የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ም/ኃላፊ የሆኑት አቶ ካሊድ አልዋን በበኩላቸው እንዳሉት የፓርቲውን አሰራርና መመሪያዎች በአግባቡ መረዳትና ለተግራዊነታቸዉ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ጠንካራ ፓርቲ የመገንባት ሂደት ዉስጥ መሰረታዊ ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም የአደረጃጀት መዋቅር ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ በፓርቲው የተዘጋጁ የተለያዩ የአሰራር መመሪያዎች አተገባበር ዙሪያ ሰነድ ቀርቦ ውይይት በማድረግ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ተሰርቷል።

ከግምገማ መድረኩ ጎን ለጎን ከሁሉም ክልሎች እና ከሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡት የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰመራ ከተማ የምዕራፍ አንድ አካል የሆነውን ኮሪደር ሙዚየም በሚል የተሰራውን የኮሪደር ልማት ስራዎች እና በክልሉ  እየተከናወኑ ያሉ የግብርና እና የሌማት ትሩፋቶችን ስራዎችን ጎብኝተዋል።

ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ እና ፅዱ ለማድረግ በሰመራ ከተማ እየተሰራ ያለዉ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገፅታ ሙሉ በሙሉ መቀየሩን እና በግብርና ዘርፍም በክልሉ የተሰሩ የልማት ስራዎች የኢትዮጵያን ብልፅግና አይቀሬነት የሚያሳዩ ተግባራት መሆናቸዉንም ጎብኚዎቹ ገልፀዋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party