Prosperity Party

"የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ባለፉት ስድስት ወራት ባከናወናቸው ስራዎች ወደ ላቀ ምዕራፍ የተሸጋገሩ ውጤቶች ተመዝገበዋል" ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር)

ጥር 03 2018 ዓ.ም

የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ በባህርዳር ከተማ  ሲያካሂድ የነበረዉ የ2018 . የመጀመሪያ ስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቀቀ።

በግምገማ መድረኩ የሁሉም ክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ 2018 . የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

የተገኙት የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ሰማ ጥሩነህ (/) በውይይቱ ላይ እንዳሉት ባለፉት ስድስት ወራት ዘርፉ ባከናወናቸው የፖለቲካና አቅም ግንባታ ስራዎች ወደ ላቀ ምዕራፍ የተሸጋገሩ ውጤቶችን ለማስመዝገብ እንደተቻለ ተናግረዋል።

የፓለቲካ ስራ ትግበራዎች ወጥ በሆነ መንገድ፣ በቅንጅት እና በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ ማከናወን መቻሉ ለሀገራዊ ሰላም፣ እድገት እና ብልፅግና የላቀ አስተዎፅኦ እንዳበረከተም አፅንኦት ሰጥተዋል።

በሚካሄዱ ውይይቶች ህዝቡን በአስተሳሰብና በተግባር ከፓርቲና ከመንግስት ጎን እንዲሰለፍ በማድረግ የሰላም ግንባታ ስራዎቻችንን ወደ አስተማማኝ ደረጃ ማድረስ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ኢትዮጵያ ከልመና እና ከተረጅነት እንድትላቀቅ በሁሉም ክልሎች ሰፊ ሥራ መሠራቱን በማስታወስ፤ ባለ ብዝኃ ዘርፍ የኢኮኖሚ እሳቤን የሚከተለው ብልጽግና ፓርቲ በሁሉም ዘርፎች ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝ ጠቅሰዉ፤ በዚህም መነሻነት ብልፅግና ፓርቲ ትናንትን፣ ከዛሬና ነገ ጋር በማሰናሰል ለትውልድ መጪዉ ትዉልድ እዳ ሳይሆን ምንዳን ማውረስ የሚያስችሉ ስኬታማ ስራዎችን አከናውኗል ብለዋል።

የኑሮ ውድነት ቅነሳ እና የስራ እድል ፈጠራ ስራዎችን በቀጣይ ወራት ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸዉ ከሚሰሩ ስራዎች መካከል እንደሆኑ በመጥቀስ ብልፅግና ፓርቲ በመጪዉ ግንቦት ወር የሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃ፣ እና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን በሚያስችል መልኩ የሚጠበቅበትን ሃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ እንደሆነም ገልፀዋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party