Prosperity Party

"የስንዴ ነዶ የመደመር፣ የአንድነት እና የመተባበር ምልክት ነው።"- አቶ ከፍያለው ተፈራ

"የስንዴ ነዶ የመደመር፣ የአንድነት እና የመተባበር ምልክት ነው።"     አቶ ከፍያለው ተፈራ 

በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣ የፓርቲውን የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማኒፌስቶና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መርሀግብር አከናውኗል።

በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኋላፊ አቶ ከፍያለው ተፈራ በፕሮግራሙ ማስተዋወቂያ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት አምስት አመታት የተገባውን ቃል በተጨባጭ ወደ ተግባር  በመቀየር ታሪክ የማይዘነጋው ስራ ሲሠራ መቆየቱን አስታውሰው፣ በሚቀጥሉት አመታትም የኢትዮጵያን ታላቅነትና አርአያነት ቀጣይ ወደ ሆነ ደረጃ ለማሸጋገርና አዲስ ታሪክ ለመስራት ሌላ ማኒፌስቶ አዘጋጅተናል ብለዋል። ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት አመታት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ የነበሩ ሁሉን አቀፍ ስብራቶችን ከመደመር ዕሳቤ በሚቀዳ ስትራቴጂ በመጠገንና በማረም ሁለንተናዊ ወደ ሆነው ብልጽግና ለማሸጋገርም ጭምር እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል። ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት የለውጥ ዓመታት አገሪቷ ከገባችበት የችግር አረንቋ ከማላቀቅ ባለፈ፣ የወደፊት ዕጣ ፈንታችን አሰተማማኝ በሆነ መሠረት ላይ ለመጣል በርካታ ልምዶች እና መልካም ተሞክሮዎች የተቀሰሙበት ጭምር እንደነበረም ገልፀዋል።

በሚቀጥሉት አምስት ዓመታትም የተመዘገቡ ስኬቶቹን አጠናክሮ በማስቀጠል ኢትዮጵያ የአፍሪካ እና የአለም አገራት ተምሳሌት እንድትሆን ለማድረግ የተያዘውን ዕቅድ እና ራዕይ ለማሳካት በሰባተኛው ዙር አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ላይ ለመወዳደር የፓርቲያችንን ማኒፌስቶ እና አርማ እያስስዋወቅን እንገኛለን ብለዋል።

በዚሁ መሠረት፣ ብልፅግና ፓርቲ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ 'ኢትዮጵያን ሁሉን አቀፍ ወደ ሆነው ተምሳሌት አገር ለማሸጋገር' የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት  በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በውጭ ግንኙነት ዘርፎች የተያዙ ዝርዝር ተግባራትን በማኒፌስቶ ውስጥ ማመላከቱንም አቶ ከፍያሌው ተናግረዋል። በተጨማሪም  ብልፅግና ፓርቲ ለ7ኛው ዙር አጠቃላይ የምርጫ ምልክቱ የስንዴ ነዶ መሆኑንም በዚሁ ፕሮግራም ላይ አስተዋውቀዋል። የስንዴ ነዶ ምልክት የመደመር፣ የአንድነት፣ የመተባበር ምልክት ሲሆን የነጻነታችን ጥንካሬና የሉዓላዊነታችን መገለጫ ዓርማ ምልክት ጭምር መሆኑንም ገልፀዋል። 

አቶ ከፍያለው ብልፅግና ፓርቲ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በፖለቲካ፣ በዕኮኖሚ፣ በማህበራዊና በውጪ ግንኙነት ዘርፎች የብልፅግናን ጉዞ የሚያረጋግጡ ዝርዝር ተግባራትን በማኒፌስቶ ውስጥ አካቶ በመፈፀም ለሕዝቡ የገባውን የተስፋ ቃል በተጨባጭ ተግባራዊ ለማድረግ የሚሠራ መሆኑንም ጠቁመው፣ ህዝባችንም በምርጫ ንቅናቄው ከመሳተፍ ጎን ለጎን ድምፁን ለብልፅግና ፓርቲ በመስጠት የኢትዮጵያንና የክልላችንን መፃኢ ዕድል አስተማማኝ መሠረት ላይ እንዲጥሉ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ ብለዋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party