“የሕዝብ ተጠቃሚነትና ተሳትፎን ማረጋገጥ የፓርቲያችን መለያ ነው” - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በምስራቅ ጉራጌ ዞን ደቡብ ሶዶ ወረዳ በኬላ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሔደ ነው።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ለተሳታፊዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)በድጋፍ ሰልፉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት የሕዝብ ተጠቃሚነትና ተሳትፎን ማረጋገጥ የፓርቲያችን መለያ ነው ነው ብለዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው የብልጽግና ፓርቲን ከሌሎች ፓርቲዎች የሚለዩ ሁለት መሠረታዊ ጉዳዮችን አንስተዋል።በዚህም የብልጽግና ፓርቲ ሰለቸኝ ደከመኝ ሳይል ቀንና ሌሊት በመስራት፣ በተለያዩ ስልቶች በገጠርና በከተማ የሚታዩ የልማት ስራዎችን በማከናወን የሕዝብን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ያለ ድርጅት መሆኑን ገልጸዋል።
በተመሳሳይ ማንኛውም የልማትና የዲሞክራሲ ስራ ያለ ሕዝብ ተሳትፎ እንደማይሳካ ገልጸው፤ ወጣቶች፣ አዛውንቶችና ሴቶች በንቃት የሚሳተፉበትን ምህዳር ፓርቲው ማመቻቸቱን አብራርተዋል።
ዶ/ር እንዳሻው አክለውም ብልጽግና በ8 ዓመታት ጉዞው እንደ ደቡብ አፍሪካው ANC እና የሞዛምቢኩ ፍሬሊሞ ካሉ አንጋፋ የአፍሪካ ፓርቲዎች ጋር የሚነጻጸር ስራ መስራቱን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያን በአለም አቀፍ ደረጃ ካሉ ቀዳሚ 20 ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ ፓርቲው በትኩረት እየሰራ መሆኑንና ለዚህም ማሳያው **COP32** የተሰኘው ትልቅ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በአዲስ አበባ እንዲካሄድ መመረጧ መሆኑን ገልጸዋል።
በመጨረሻም ለወረዳው ነዋሪዎች በመልዕክታቸው ምርጫው ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ እንዲሆን የአካባቢያቸውን ሰላም እንዲጠብቁ እናም ግንቦት 24 በሚካሄደው ምርጫ የብልጽግና ፓርቲን በመምረጥ የጀመረውን የልማትና የብልጽግና ጉዞ እንዲያፋጥኑ ጥሪ አቅርበዋል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን ባስተላለፉት መልዕክት፤ የለውጡ መንግስት ባለፉት ስምንት ዓመታት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ዘርፎች በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ገልጸዋል።
ለበርካታ ዓመታት የህዝብ ጥያቄ የነበረው የዞን አደረጃጀት ጥያቄ በለውጡ መንግስት ምላሽ ማግኘት ዞኑ በሁሉም መስክ ያለዉን ኦምቅ አቅም እንዲጠቀም አስችሎታል ብለዋል።
በዚህም ዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከክልሉ ዞኖች በምሳሌነት የሚጠቀስ ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝም አብራርተዋል።
በመጨረሻም አስተዳዳሪው ህዝቡ ለተገኘው ሰላም እና ልማት እውቅና በመስጠት ከብልጽግና ፓርቲ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።
#prosperity