Prosperity Party

‎"ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ አስተዳደር 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ቅስቀሳን በማስመልከት የእግርኳስ ጨዋታ ተደረገ

በዛሬው ዕለት በአስተዳደሩ ወረዳ 02 ሳቢያን ሜዳ እና በወረዳ 08 አስታጥቄ ሜዳ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ አካል የሆነው የብልፅግና ዋንጫ የእግር ኳስ ጨዋታ ውድድር በድምቀት ተካሄደ።

‎በወረዳ 02 ሳቢያን ሜዳ በተደረገው የቅስቀሳ መርሃ ግብር ላይ የአስተዳደሩ ክቡር ከንቲባ አቶ አድር ጁሃርን ጨምሮ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ደረጀ ፀጋዬ እና የፓርቲው አባላትን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

‎በተመሳሳይ በወረዳ 08 ለገሀሬ አስታጥቄ ሜዳ በተከናወነው መርሃ ግብር ላይ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ፣ የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ እንዲሁም የንግድ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ፣ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ፅ/ቤት ምክትል እንዲሁም የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሻኪር አህመድ፣ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ፅ/ቤት ልዩ ረዳት አቶ ዮናስ ጥግነህ እና ሌሎች የመንግስትና የፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ታድመውበታል።

በዝግጅቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ላይ ሀገርን ወደ ላቀ እድገት ለማሻገር መልካም ተግባራትን ለማስቀጠል ብልፅግና እየሰራ ያለውን ስራ ፓርቲው ለድሬዳዋ እድገትና ለኢትዮጵያ ከፍታ እየሰራ እንደሚገኝም ተጠቅሷል::

#Prosperity

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party