Prosperity Party

‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የአፍሪካ እና የዓለም አቀፍ መሪዎችን ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደኅና መጣችሁ በማለት፣ የአፍሪካን ታሪካዊ ዐሻራ እና ጽኑ ርዕይ አፅንዖት ሰጥተው ገልጸዋል።

‎የአህጉሪቱ ትልቁ ሀብት የተፈጥሮ ጸጋ ብቻ ሳይሆን፣ ጠንካራ ተቋማትን የመገንባት፣ ፈጠራን የማሳደግ እና ለዘላቂ ልማት ያለው አስተዳደራዊ ችሎታ መሆኑን አሳስበዋል። በውኃ ልማት፣ በኢነርጂ፣ በምግብ ዋስትና እና በኢንዱስትሪ ልማት ረገድ እየታዩ ያሉ መሻሻሎችን በማንሳት፤ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ በስንዴ ምርት ራስን የመቻል ጥረትን እና እየተስፋፉ ያሉ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንቶችን ለአፍሪካዊ መፍትሔዎች እና ለጋራ ብልጽግና ማሳያ ተጨባጭ ምሳሌዎች አድርገው ጠቅሰዋል። 

‎አኅጉሩ የደረሰበት ጠንካራ የዕድገት ጉዞ፣ የኢትዮጵያን የ10.2% ተጠባቂ ዕድገት፣ እንዲሁም የአኅጉሩን የስነ-ሕዝብ ብልጫ ለመጠቀም በወጣቶች፣ በጤና እና በትምህርት ላይ ኢንቨስት ማድረግ ያለውን አስፈላጊነት ገልጸዋል።

‎በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር አማካኝነት የሚታየውን የአየር ንብረት መሪነት፣ በ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ሥር እየተከናወነ ያለውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የታዩ ስኬቶችን እና የአኅጉራዊ ትስስር መስፋፋትን አጉልተዋል። 

በመጨረሻም ዓለም አቀፋዊ አጀንዳዎችን የመቅረጽ አቅም ያለው እና ለሁሉም አፍሪካውያን የሚተርፍ፤ ልማትን፣ ዕድልን እና ክብርን የሚያረጋግጥ በራሱ የሚተማመንና የተባበረ የአፍሪካ ሕብረት እንዲኖር ጥሪ በማቅረብ ንግግራቸውን አጠቃለዋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party