Prosperity Party

ጠንካራ ተቋም ለመገንባት የሚያስችል መሰረታዊ የሆኑ አቅሞች በኮሚሽኑ ተፈጥሯል- የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ደስታ ተስፋው (ዶ/ር)

የብልፅግና የኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን ዋና ፅ/ቤት ለክልሎች፣ ለከተማ አስተዳደር፣ ለፌዴራል ተቋማት አደረጃጀት ብልጽግና የኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን አባላት እና ለዞን፣ ልዩ ወረዳና ከተማ ቅ/ጽ/ቤት አመራሮች 6ኛ ዙር ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መድረክ በአዳማ መካሄድ ተጀመረ።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ደስታ ተስፋው (ዶ/ር) እንደተናገሩት የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ተቋም ለመገንባት የሚያስችል ቁመና ላይ መድረሱን ጠቅሰዋል።
ለተቋም ግንባታ ግባችን ስኬት ኮሚሽኑ በየጊዜው በየደረጃው ለሚገኙ የኮሚሽኑ አመራሮችና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን እያዘጋጀ ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
ለሰልጣኞች በተለያዩ ርእሶች ዙሪያ የሚቀርቡ የስልጠና አጀንዳዎች ለቀጣይ ተልዕኮ የሚያዘጋጅ መሆናቸውን ኮሚሽነሩ ጨምረው ገልፀዋል።
የኮሚሽኑ ፀሐፊና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲው ጽ/ቤቶች አደረጃጀቶችና አካላት አመሰራረት፣ ተግባርና ሀላፊነቶች ግልፅነት ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል።
ስራዎችን ተጠያቂነት ባለው መልኩ በማስቀጠል ጠንካራ እና ተፅእኖ መፍጠር የሚችሉ የፖርቲ አደረጃጀት እንዲኖር መሰራት እንደሚገባው ገልጸዋል።
ስልጠናው ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party