ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ጋር ተወያዩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ለይፋዊ ጉብኝት የመጡትን የእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግን ተቀብዬ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
የኢትዮጵያ እና እስራኤልን ግንኙነት በማጤን በወል ፍላጎታችን ላይ ተመስርተን ትብብራችንን የምናሳድግባቸውን መንገዶች ተመልክተናል ሲሉም ገልጸዋል።