የፓርቲ አሰራር እና መርሆችን ተከትሎ በመስራት ሂደት ዉስጥ የሚያግጥሙ ውስንነቶችን የመፍታት ባህል እያደገ መምጣቱ ተገለፀ
ጥር 20 2018 ዓ.ም
የብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽን እና ስነምግባር ኮሚሽን፥ የኮሚሽን የኢንስፔክሽንና የቁጥጥር አሠራር ሥርዓት ላይ ስልጠና ሰጥቷል።
የብልጽግና የኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን በመተዳደሪያ ደንብ በተሰጠው ሀላፊነት መሰረት ከህብረት ጀምሮ በየደረጃው የፓርቲ ጽ/ቤቶች የፓርቲ የአደረጃጀትና አሰራር መርህን ተከትሎ የሚፈጠሩ ውስንነቶችን የመፍታት ባህል እያደገ መምጣቱን የኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን የሥነ-ምግባር ዋና ዳይሬክተር አቶ ነስረዲን መሐሙድ ገልፀዋል።
በፓርቲያችን ውስጥ የሚያጋጥሙ የአፈጻጸም ውስንነቶችን በፓርቲው መዋቅር፣ መመሪያና አሰራር መርሆዎች ላይ ተመስርቶ የመፍታት ባህል ማዳበር ለሀገር ግንባታና ለፓርቲው ጥንካሬ ወሳኝ እንደሆነ ተናግረዋል።
ጠንካራ ፓርቲን ለመገንባት እየተደረገ በሚገኘው ጥረት ኮሚሽኑ ሀላፊነቱን ለመወጣት እንዲቻለው የኢንስፔክሽንና ቁጥጥር አሰራርን ተከትሎ በተደራጀ መልኩ ተግባራቱን መፈፀም እንዳለበት ጠቅሰዋል ።
አቶ ነስረዲን አክለውም፤ የፓርቲው መዋቅር ካለው ግዝፈት አኳያ በሁሉም ቦታዎች የሚፈለገውን ግኝት በማምጣትና ክትትል የማድረግ በርካታ ስራዎች እየሰራ እንደሆነ ገልፀዋል ።
ስለሆነም ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመታገል የትግል አጀንዳ የማድረግ ስራ የሁሉም አመራር እና አባላት ስራ ስለሆነ አጠናክረን ልንሰራ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በየደረጃው የሚገኙ የኮሚሽኑ መዋቅሮች በኢንስፔክሽን የተገኙ ጥንካሬዎችን በማስፋትና በጉድለት የተለዩትን በማረም ለጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ግባችን ስኬት ተግተን መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።