የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ "የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ" መድረክ ላይ ያስተላለፉት መልእክት
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አድማሱ ዳምጠው ''የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ'' በተሰኘው የዘርፉ የምክክር መድረክ ላይ በሚዲያው ዘርፍ የለውጡ መንግስት ያስመዘገባቸው ስኬቶችን ለተቋሙ ያለውን አበርክቶ በጥልቀት አቅርበዋል።
ተቋሙ ሰፊውን ሪፎርም በመቀላቀል ብቁ፣ ተወዳዳሪና ሙያዊ ነጻነቱ የተከበረ ማድረግ ችሏል።
በይዘት፣ በተለወጠ አደረጃጀት እና በቴክኖሎጂ አማራጮች ተደራሽ በመሆን ተወዳዳሪነቱን አስፍቷል። ተቋሙ ከሪፎርሙ በመቋደሱ ከራሱ አልፎ ሰፊ የብሮድካስት ልምዱን በማካፈል ላይ ይገኛል። በተጨማሪም ፈጠራን፣ የሀሳብ ብዝሀነትና አለም አቀፋዊነትን በማስፋት ተመራጭና ወቅታዊ የመረጃ ምንጭ በመሆን እያገለገለ ይገኛል።
#PMOEthiopia