የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ «መደመር» መጽሐፍ በቻይንኛ ተትርጉሞ፤ በቅርቡ ለንባብ ይበቃል!
በ2010 ዓ.ም የነበረውን ሀገራዊ ለውጥ ተከትሎ የኢትዮጵያ የነገ ጉዞ ፍኖተ-ካርታ ሆኖ የተወለደውና በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የተጻፈው የ«መደመር» መጽሐፍ፣ ኦፊሴላዊ የቻይንኛ ቋንቋ ትርጉም ሥራው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፤ በቅርቡም ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለንባብ ሊበቃ መሆኑ ተረጋገጧል።
ባለፉት አሥርት ዓመታት ከአፍሪካ አህጉር ፈልቀው ወደ ዓለም መድረክ ከተሻገሩ ጥቂት አገር በቀል ፍልስፍናዎች መካከል ግንባር ቀደሙ የሆነው «መደመር»፣ አሁን ላይ ተደራሽነቱና ይህን የኢትዮጵያ አገር በቀል የሆነው የመደመር ፍልስፍና በርካቶች በትኩረት የሚመለከቱት አጀንዳ እየሆነ ነው። ቻይና የትርጉም ሥራውን እያጠናቀቀች ባለችበት በዚህ ወቅት፣ መጽሐፉ ከዚህ ቀደም በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በእንግሊዝኛ ካለው ተደራሽነት በተጨማሪ በቅርቡ በአረብኛ እና በፓኪስታን የኡርዱ ቋንቋዎች ተተርጉሞ በደማቅ ሁኔታ መመረቁ ይታወሳል። አሁን ደግሞ በቢሊዮኖች የሚነገርለትን የቻይናን መድረክ በይፋ ለመቀላቀል የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ይገኛል።
ይህ የ«መደመር» መጽሐፍ ወደ ቻይንኛ ቋንቋ መተርጎም እና አሁን ላይ ሀያል ከሆኑ አገራ መካከል የምትጠቀሰውን ቻይናን ትኩረት ማግኘቱ ከመጽሃፍ ትርጉም ሥራ ባለፈ በርካታ ስትራቴጂካዊ እና ፖለቲካዊ እንድምታዎችን ይዟል፡፡ እንደ ቻይና ዓይነት እጅግ የዳበረ፣ የረጅም ዘመን የፖለቲካ ፍልስፍና ታሪክ ያላት እና ከማኦ ዜዱንግ እስከ ዴንግ ዚያኦፒንግ፣ አሁን ደግሞ እስከ ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ የዘለቀ የራሷ የርዕዮተ-ዓለም መስመር ያላት ሀገር፣ "መደመር"ን ኦፊሴላዊ በሆነ መንገድ ወደ ራሷ ቋንቋ መተርጎሟ፤ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪና ትኩረት ሳቢ ፍልስፍና ማበርከት መቻሏን ማረጋገጫ ነው ። ኢትዮጵያ ባለፉት ዘመናት ከውጭ የሚመጡ ርዕዮተ-ዓለሞችን (Capitalism/Socialism) ስታስተናግድ የኖረችበትን የታሪክ ምዕራፍ በመቀየር፣ አሁን ግን የራሷን አገር በቀል ፍልስፍና ወደ ውጭ የምትልክ ሀገር ለመሆኗ ትልቅ ማሳያ ነው መደመር መጽሃፍ ።
መጽሐፉ አፍሪካን፣ መካከለኛው ምስራቅን (በአረብኛ)፣ ደቡብ እስያን (በኡርዱ) እና አሁን ደግሞ ምስራቅ እስያን (በቻይንኛ) ተደራሽ ማድረጉ፣ ፍልስፍናው ከተወለደበት የኢትዮጵያ ምድር ተሻግሮ አህጉራትንና የተለያዩ ባህሎችን የማስተሳሰርና የማቀራረብ ትልቅ የዲፕሎማሲ አቅም እንዳለውም ማሳያ ነው ።
የመደመር መጸሃፍ የቻይንኛ ትርጉም በቅርቡ ይጠብቁ!
#prosperity