የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ለሁለንተናዊ ብልፅግና ጉዞአችን እመርታ !
ጥር 02 2018 ዓ.ም
የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ የ2018 ዓ.ም የስድስት ወራት አፈፃፀሙን ከቅርንጫፍ ፅ/ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ አመራሮች ጋር በጋራ ግምገማ አካሂዷል።
የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስቴር አቶ መለሰ አለሙ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት ባለፉት ስድስት ወራት በዴሞክራሲ ባህል ግንባታው ላይ ዘርፈ ብዙ ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቅሰው በግምገማው የነበሩ ክፍተቶችን ማረም የሚያስችል ፣ ውጤቶችን የሚያጠናክር የጋራ ተግባቦት እንደሚፈጠርበት አመላክተዋል።
ግምገማዊ ውይይቱ የዲሞክራሲ ባህል ግንባታውን ለማጠናከር ፣ የሴቶች ተሳትፎና አበርክቶን ለማላቅ ፣ የወጣቶች ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ለማሳደግ ፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ወደ ባህል ለማሸጋገር ፣ የውይይትና ምክክር ባህልን ለማዳበር ልዩ ትኩረት እንደሚያደርግም አቶ መለሰ ጠቁመዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ከጥልቅ ጉስቁልና እየወጣች የብልፅግና ተምሳሌት እየሆነች በምትገኘው አዲስ አበባ የሚካሄደው ግምገማዊ ውይይቱ ለጋራ ድል ተጨማሪ ተነሳሽነትን እንደሚፈጥር አስረድተዋል።
የፓርቲያችንን አሻጋሪ እሳቤዎች ቀን እና ሌት በመትጋት ተግባራዊ በማድረግ ድሎችን ለማብዛት ፣ የዴሞክራሲ ምህዳሩንም ይበልጥ ለማስፋት የሚደረገው ርብርብ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቶ ሞገስ ጠቅሰዋል።
በግምገማዊ ውይይቱ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስቴር አቶ መለሰ አለሙ ፣ የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ም/ኃላፊ ሚኒስቴር ዲኤታ አቶ አለማየሁ እጅጉ ፣ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ም/ፕሬዝዳንትና የጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መስከረም አበበ ፣ የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ም/ፕሬዝዳንትና የጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ኦባንግ ኩመዳንን ጨምሮ የሁሉም ክልሎች እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊዎችና ምክትል ኃላፊዎች ተገኝተዋል።