የእኔ ሃሳብ የሀገሬን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ይወስናል ብለን በማመን በንቃት እንሳተፍ!
ብልጽግና ፓርቲ በሀገራችን ለዘመናት የተከማቹ ቁርሾዎችንና የፖለቲካ ቅራኔዎችን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት የተለያዩ ስትራቴጂ በመንደፍ ሲሰራ ቆይቷል።
የኢትዮጵያን የብሄር፣ የሃይማኖት፣ የባህል፣ የቋንቋን ብዙሃነትን በአግባቡ ማስተናገድ የሚችል አውድ በመፍጠር እና ወንድማማችነትና እህትማማችነትን በማጉልበት ሀገራዊ አንድነትን ማጠናከር ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡
ከዚህም አንጻር ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያሳተፈ ውይይት በማካሄድ ቁርሾዎችን ከመሰረት የሚነቅሉ የጋራ የስነ-ልቦና አንድነትን መፈጠር እና ማህበራዊ ትስስርን ማጎልበት ያስፈልጋል።
በክቡር የፓርቲያችን ፕሬዘዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው “በይቅርታ እንሻገር፣ በፍቅር እንደመር” የሚለው መርህ፣ ልዩነቶችን በሃይል ሳይሆን በውይይትና በንግግር ለመፍታት በሽብርነተኝነት ተፈርጅው የነበሩ የፓለቲካ አመራሮች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ በሀገራቸው ጉዳይ ተሳታፊ እንዲሆኑ እድል ፈጥሯል፡፡
በተጨማሪም የነጠላና የአግላይነት ትርክትን በመቀየር ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያካተተ አሰባሳቢ የወል ትርክትን ለመገንባት በየደረጃው ውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ውስብስብ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት የበለጸገች ለሁሉም የምትመች ሀገር ለመፍጠር ወይይቱ ተቋማዊ በሆነ መንገድ በመመራቱ ውጤት እያስመዘገበ ነው፡፡
በዚህም ረገድ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሁሉም አካባቢዎች፣ ከሁሉም ማንነቶች፣ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የተሰበሰቡ ስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ኢትዮጵያውን በጋራ መክረው የጋራ ነጋቸውን የተሻለ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡
ከ1 ሺህ 300 በላይ ወረዳዎች የተውጣጡ 4 ሺህ ሰዎች በሚሳፉበት በዚህ የምክክር መድረክ በንቃትና በባለቤትነት ስሜት መሳተፍ ለዚህ አገራዊ አጀንዳ ስኬት መሰረቱ ነው።
የምክክሩ ግብ ሊሳካ የሚችለው እያንዳንዱ ዜጋ ሂደቱን የራሱ አድርጎ ሲወስደውና የእኔ ሃሳብ የሀገሬ የወደፊት ዕጣ ፈንታን ይወስናል ብሎ በማመን በምክንያታዊነትና እውነትን መሠረት በማድረግ በትዕግስትና በመቻቻል መወያየት ሲቻል ነው፡፡
#prosperity