የአዋሽ ኤፍ ኤም ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር አብዱ መሀመድ ''የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ'' በተሰኘው ሀገራዊ የምክክር መድረክ ላይ የለውጡ መንግሥት ለዘርፉ ያበረከታቸውን ትሩፋቶች አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጡ
የአዋሽ ኤፍ ኤም ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር አብዱ መሀመድ ''የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ'' በተሰኘው ሀገራዊ የምክክር መድረክ ላይ የለውጡ መንግሥት ለዘርፉ ያበረከታቸውን ትሩፋቶች አብራርተዋል። የቁጥጥር እና የፖለቲካ ገደቦች፣ የአቅምና የሙያ ክፍተቶች፣ የፋይናንስና የቴክኖሎጂ ገደቦች ዘርፉንና ተቋሙን ሲፈትኑ የከረሙ ስር የሰደዱ ችግሮች እንደነበሩ አንስተዋል። እነዚህ ችግሮች የፖሊሲ እና የህግ ማሻሻያዎችን በማድረግ፣ ለኢንቨስትመንት ትኩረት በመስጠት የሬዲዮ ጣቢያዎች ከመበራከታቸው ባለፈ የጋራ እሴቶችን በማጠናከር እና ማህበረሰብን በማስተሳሰር እንዲሁም ሀገርን በመገንባት ሂደት ውስጥ ወሳኝ ሚናቸውን እንዲጫወቱ አስችሏል።
#PMOEthiopia