Prosperity Party

የአርጆ ዲዴሳ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት መጠናቀቂያው ተቃርቧል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ግንባታው እየተፋጠነ የሚገኘው የአርጆ ዲዴሳ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት ሊጠናቀቅ መቃረቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የአርጆ ዲዴሳ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት መጎብኘታቸውንና የደረሰበት ደረጃም አስደናቂ መሆኑን መመልከታቸውን ገልጸዋል።

ይኽ ትልቅ ፕሮጀክት በቅርብ ዓመታት ግንባታው ተፋጥኖ ወደ መጠናቀቂያው መቃረቡን ጠቁመዋል። 

ለአገልግሎት በሚበቃበት ጊዜም የተለያዩ የአዝርዕት ልማትን በመደገፍ እንደ ሀገር የተጀመረውን የምግብ ሉዓላዊነት ጥረቶች እና በሺዎች የሚቆጠሩ አርሶአደሮችን በመጥቀም ግብርናውን እንደሚያሻግር ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ ባላሰለሰ ጥረት እና የታቀደለትን ግብ በማሳካት የአካባቢውን ማኅበረሰብ ኑሮ ከፍ እንደሚያደርግ እምነታቸውን ገልጸዋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party