Prosperity Party

የታዳሽ ኃይል ልማት እና የኤኔርጂ ሉአላዊነት ማረጋገጥ የብልፅግና ፓርቲ ቁልፍ የትኩረት አቅጣጫ ነው-ሳምንታዊ መልዕክት

ብልፅግና ፓርቲ የታሪክ እጥፋት ከፈጠረባቸው ዘርፎች የታዳሽ ኃይል ልማት እና የኤኔርጂ ሉአላዊነት ማረጋገጥ አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ ለዚህም ሁለት መነሻዎች አሉት፡፡ አንደኛው ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል እምቅ አቅሟ መጠቀም እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የበካይ ኃይል ተፅእኖ እና የጥገኝነት አደጋ መቀነስ የግድ ስለሚል ነው፡፡ የበካይ ኃይል ተፅእኖና የጥገኝነት አደጋ የሀገር ብሔራዊ ጥቅም፣ ሉአላዊነት እና የተፈጥሮ አጠቃላይ ህልዉና እስከመገዳደር የሚደርስ በመሆኑ የሀገራት ብሔራዊ ደህንነት አጀንዳ እስከመሆን ይደርሳል፡፡ በተለይ ነዳጅ የመሳሳሉ የበካይ ኃይል አቅርቦቶች በከፍተኛ ሁኔታ እየተስተጓጎሉ ባሉበት በአሁኑ ጊዜ ዓለም ወደ ታዳሽ ኃይል ፊቱን ማዞር ተጨማሪ ግድ የሚለው ምክንያት እየሆነ ይገኛል፡፡
ከዚህ አንጻር ሀገራችን ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ልማትና የኤኔርጂ ሉአላዊነት ለማረጋገጥ ቀድም ብላ የቤት ሥራዎቿን መሥራት ጀምራለች፡፡ ይህ ጅማሮ በለውጡ መንግሥት ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት ወደ ላቀ ደረጃ እየደረሰ ይገኛል፡፡ በዚህ መሠረት የኢትዮጵያ ዕምቅ አቅም እና የመበልጸግ መሻት ግምት ወስጥ ያስገባ እንዲሁም የዓለም የነዳጅና ሌሎች በካይ ኃይል ላይ ሊፈጠሩ የሚችሉ መስተጓጎሎች የተነበየ ተግባራዊ እርምጃ እየተወሰደ ቆይቷል፡፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የዚህ ቁርጠኝነት ቀዳሚ ማሳያ ሲሆን ባለፈው ሳምንት የተመረቀው የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት እና በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የተገነባው ግዙፉ የጸሀይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ለዘርፉ የተሰጠውን ትኩረት እና የቀድሞ መዘጋጀት ተግባር ሁነኛ ማሳያ ነው፡፡
ብልፅግና ፓርቲ ባለፈው ምርጫ ላይ የታዳሽ ኃይል እና የኤኔርጂ ሉአላዊነት ጉዳይ በማኒፌስቶው በግልፅ በማስቀመጥ ለህዝብ የገባውን ቃል በተግባር ሲገልጥ ቆይቷል፡፡ በዘንድሮው ምርጫም ለዘርፉ ዘመኑን በዋጀ ትኩረት በመሥጠት በማኒፌስቶው ላይ አካትቶታል፡፡ በዚህ መልኩ ቃል እና ተግባር የአንድ ሳንቲም ገጽታዎች እንዲሆኑ በማድረግ ኢትዮጵያ በእምቅ አቅሟ፣ በመብልጸግ መሻቷ እና ለዓለም ማበርከት ባለባት አስተዋጽኦ ልክ ታዳሽ ኃይልና የኤኔርጂ ሉአላዊነቷን እየረጋገጠች     ትገኛለች፡፡ ይህ ተግባር ታዳሽ ኃይልን ለራስዋ ከመጠቀም አልፋ ጎረቤት ሀገራትን በኃይል፣ በኃይል መሰረት ልማት እና በንግድ ማስተሳሰር መጀመርዋ አያሌ ብሔራዊ፣ ቀጣናዊና ዓለምአቀፋዊ ጥቅሞች እንድታገኝ አስችሏታል፡፡ 
የዚህ ማሳያ ስለዓለም አየር ንብረት የሚመክረው ታላቁ የኮፕ-32 ጉባኤ አትዮጵያ እንድታዘጋጅ ተመርጣለች፡፡ ይህም የዕሳቤ፣ መርህ እና ተግባር ድምር ውጤት ማሳያ ነው፡፡ 
ይህ ሁሉ ተደምሮ የኢትዮጵያ ብልፅግና አይቀሬ እና በአስተማማኝ ሀዲድ እየገሰገሰ መሆኑ ህያው ምስክር አድርጎታል፡፡ ይህም ብልፅግና በታዳሽ ኃይል የተሞላችና የበለጸገች ሀገር ለመገንባት ቀጣይ የህዝብ ይሁንታ ማግኘት የሚገባው ትክክለኛ ፓርቲ ያደርገዋል፡፡ 
ብልፅግና ፓርቲ

ሚያዝያ 19፤ 2018 ዓ/ም

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party