Prosperity Party

የተቋም ግንባታ ሥራችን ለሁለንተናዊ ብልፅግና ራዕይ እዉን መሆን ወሳኝነት አለው- ሳምንታዊ መልዕክት

ብልፅግና ፓርቲ ሀገራዊ ለዉጡን ተከትለው ከመጡ ተቋማት መካከል አንዱና ዋነኛው ነው፤ ብልፅግና በኢትዮጵያ የመድብለ ፓርቲ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ወጥ፣ ዉሁድ እና በትክክል ኢትዮጵያን የሚመስል ተደርጎ የተፈጠረ ሀገራዊ ተቋም ነው፡፡ ፓርቲው የቆዩን ሰው ወለድ እና ሥርዓታዊ ሥብራቶችን ለመጠገን አዳዲስ ዕሳቤዎች፣ አሠራሮች እና ስትራቴጂዎች ያስተዋወቀ ፓርቲ ነው፡፡ እነዚህ ስትራቴጂዎች ወደ መሬት ወርደው ህዝብን እንዲጠቅሙ ለማስቻል እስካሁን አያሌ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ በነዚህ ጥረቶችም በሀገር ብቻ ሳይሆን በዓለም ደረጃም ጎልተው የወጡ ዘርፈ ብዙ ውጤቶችና እመርታዎች መፍጠር ተችሏል፡፡

ፓርቲው የመደመር ዕሳቤን ማስተዋወቅና በምልአት መተግበር የቻለ ሲሆን የዕሳቤው ትግበራ እዉን ለማድረግ ሰፊ ዕቅድ አዘጋጅቷል፡፡ ዕቅዱ በሩቅ-ዕይታ የተቃኘና አስተማማኝ መሠረት ላይ የጸና እንዲሆን ተደርል፡፡ ከዚህ በመነሳት በሀገራችን ፖለቲካ ፓርቲዎች ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የ10 ዓመት ዕቅድ በመንደፍ ሥራዎች በዕቅድ እንዲመሩ እና በውጤት እንዲለኩ አስችሏል፡፡

የዚህ የረዥም ጊዜ ዕቅድ አካል የሆነውን የያዝነው ዓመት ዕቅድ “ከውጤት ወደ ደረጃ ማላቅ/standardization” የሚል አቅጣጫ ተቀምጦ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ የያዝነው ዓመት የዴሞክራሲ እመርታ የሚመመዘገብበት የምርጫ ዓመትም እንደመሆኑ መጠን ሂደቶችና ሥራዎች በላቀ ደረጃ መፈጸም እንዳለባቸው አቅዶና አቅጣጫ አስቀምጦ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ይህንን ለማሳካትም በዓመቱ የሚሰራው የፓርቲና መንግሥት ሥራ የቀጣይ አምስት ዓመታት ሂደትን የሚወስኑ መሆናቸው በመገንዘብ ሥራዎች በልዩ ትኩረት፣ ብቃት ርብርብ እንዲመሩና እንዲተገበሩ ተደርገዋል፡፡

በዚህ መሰረት ፓርቲው የ9 ወር የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ያካሄደ ሲሆን በግምገማ መድረኩ አሁናዊ ሁኔታዎች ግምት ውስጥ በማስገባት በዕቅድ የተያዙት ሥራዎችን በጥልቀት ፈትሿል፡፡ በዚህም የፓርቲው የ9 ወራት አፈጻጸም በዕቅዱ እና ከዛ በላይ የሆነ አፈጻጸም መመዝገቡን ተመልክቷል፡፡

ግምገማው ብልፅግና ፓርቲ የደረሰበትን ከፍተኛ ተቋማዊ አቅም ያሳየ ሆኗል፡፡ ግምገማው ፓርቲው በኢትዮጵያ የመድብለ ፓርቲ ዕድገት ላይ እየተጫወተው ያለዉን አይተኬ ሚና ከማሳየት ባሻገር ያነገበዉን ሁለንተናዊ ብልፅግና እዉን ለማድረግ ትልቅ ተስፋ የፈጠረ መሆኑም አረጋግጧል፡፡ የፓርቲው አሁናዊ ተቋማዊ አቅም ለሀገራዊና ዓለምአቀፋዊ ፓርቲዎች የሚያስተላልፈው መልዕክት ያለ ሲሆን ይህም ሀገር ለማሻገርና ለማበልጸግ የአቃፊነትና ህብረብሄራዊነት ዕሴቶች ትልቅ መደላድል መሆናቸውን ነው፡፡ 

ከዚህ በተጨማሪ ሀገራዊ ተቋማት በኢትዮጵያ ልክ የተደራጁ፣ የዕሳቤና የአሰራር ልህቀት የተላበሱ እና ህዝብን ማዕከል አድርገው የሚሰሩ ከሆኑ የምንመኘውን ሁለንተናዊ ለውጥ እዉን ለማድረግ አስተማማኝ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡

ተቋማዊ አቅም ለሀገር ግንባታ መሰረት ነው፤

የተቋም ግንባታ የሁላችንም ድርሻ የሚጠይቅ በመሆኑ ሁላችንም ሚናችን ማበርከታችን እንቀጥል፤

ብልፅግና ፓርቲ

ሚያዝያ 12፤ 2018 ዓ/ም

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party