የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ በዶሎ አዶ ወረዳ በደመቀ ሁኔታ ተካሄደ
“ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!” በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ በሊባን ዞን ዶሎ አዶ ወረዳ በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ የሶማሊ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ ኢ/ር መሀመድ ሻሌ ባስተላለፉት መልእክት ብልጽግና ፓርቲ ከትላንት ድሎች ይልቅ የነገውን ታላቅ ህልም ለማሳካት በቆራጥነት እየሰራ ሲሆን፣ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር በገባው አዲስ ቃል ኪዳን ጉዞውን አጠናክሮ ቀጥሏል ብሏል::
ብልጽግና ፓርቲ በሁሉም ዘርፎች ስኬቶችን በማስመዝገብ የሀገሪቱን የሽግግር ጉዞ እያሳካ ይገኛል። በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የተጀመረው ለውጥ በፅኑ መሰረት ላይ እንዲቆም እና ኢትዮጵያ የብልጽግና ተምሳሌት ሆና እንድትገነባ ፓርቲያችን ሌት ተቀን ይሰራል።
በመጨረሻም፣ ለቀጣዮቹ ዓመታት ኢትዮጵያን ወደ ተሟላ ብልፅግና ለማሸጋገር የህዝቡ ትብብር ወሳኝ መሆኑን በመግለጽ፣ መላው የዶሎ አዶ ህዝብ የልማት ምልክት የሆነውን "የስንዴ ነዶን" እንዲመርጥ ጥሪ ቀርቧል።
ብልፅግና ፓርቲን ይምረጡ!
ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነዉ!
#prosperity