Prosperity Party

የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ በቦረና ዞን ያቤሎ ከተማ በደመቀ ሁኔታ ተካሄደ

“ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!” በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ በቦረና ዞን ያቤሎ ከተማ በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ክቡር አቶ ሳዳት ነሻ፣ ባስተላለፉት መልእክት ብልፅግና ፓርቲ የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ የለውጥ ኃይል መሆኑን በመግለጽ በተለይም የሁሉንም ህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚነት በፍትሃዊነት ከማረጋገጥ አንጻር በዝናብ እና በከብት እርባታ ላይ ብቻ ጥገኛ ሆኖ የነበረውን አርብቶ አደር ከዚህ ጥገኝነት በማላቀቅ የመስኖ ልማት ተጠቃሚ እንዲሆን መደረጉን ገልጸዋል። ይህም ማህበረሰቡ ምርታማነቱን በመጨመር እራሱን እንዲችል ትልቅ እገዛ ማድረጉን ጠቁመዋል።

የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመቋቋም በተከናወኑ ተግባራት ላይም፣ በተለይም በቦረና ዞን 14 ግዙፍ የውሃ ማቆሪያ (ፊና) ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለአገልግሎት መብቃታቸውን አቶ ሳዳት አንስተዋል። እነዚህ ፕሮጀክቶች አርብቶ አደሩንና ከብቶቹን ከድርቅ አደጋ በመታደግ ረገድ የጎላ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙና በቀጣይም ድርቅን በዘላቂነት ለመቋቋም የሚያስችሉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
በተጨማሪም እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያሉ ግዙፍ ብሔራዊ ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውን፣ የጤና መድህን አገልግሎት መስፋፋቱን እንዲሁም የ“ቡኡራ ቦሩ” እና “ኢፋ ቦሩ” ትምህርት ቤቶች ግንባታ የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጣቸውን ጠቅሰዋል።
የቦረና ዞን አስተዳዳሪ አቶ አብዱሰላም ዋርዮ በበኩላቸው፣ ብልጽግና ፓርቲ በአስቸጋሪ የአየር ንብረት ለውጥ ወቅት ከህዝቡ ጎን በመሆን የድርቅ መቋቋሚያ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸዋል። በምርጫ ቅስቀሳው ወቅት ተሳታፊዎች የቦረና ዩኒቨርሲቲን፣ አዳዲስ ሆስፒታሎችንና የልማት ፕሮጀክቶችን የጎበኙ ሲሆን፣ ልማቱ እንዲቀጥል ለፓርቲው ያላቸውን ድጋፍ አረጋግጠዋል።
በመጨረሻም፣ ለቀጣዮቹ ዓመታት ኢትዮጵያን ወደ ተሟላ ብልፅግና ለማሸጋገር የህዝቡ ትብብር ወሳኝ መሆኑን በመግለጽ፣ መላው የቦረና ህዝብ የልማት ምልክት የሆነውን "የስንዴ ነዶን" እንዲመርጥ ጥሪ ቀርቧል።
ብልፅግናን ይምረጡ!
ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው!

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party