የብልፅግና ፓርቲ የምረጡኝ ቅስቀሳ በኦሮሚያ!
"ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌታዊ ሀገር የማሸጋገር ጉዞ"
የብልፅግና ፓርቲ "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!" በሚል መሪ ቃል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ በኢሉ አባ ቦር፣ በምስራቅ፣ በምዕራብ እና በሰሜን ሸዋ ዞኖች ሰፊ የሕዝብ ንቅናቄ የተፈጠረበት የምረጡኝ ቅስቀሳ አካሄደ።
በኢሉ አባ ቦር ዞን ባቾ ወረዳ በተካሄደው መርሃ-ግብር ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነመራ ቡሊ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ብልፅግና አገሪቱን ካጋጠማት የመፍረስ ስጋት ታድጎ ወደ ተሻለ ምዕራፍ እያሸጋገራት ያለና ለሕዝብ የገባውን ቃል በተግባር እየፈጸመ የሚገኝ "የተግባር ፓርቲ" መሆኑን አብራርተዋል። በአሁኑ ወቅት በሁሉም ዘርፎች የተጀመሩ ሁለንተናዊ ለውጦችን ዳር ለማድረስና ኢትዮጵያን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የፓርቲው ምልክት የሆነውን የስንዴ ነዶ በመምረጥ ሕዝቡ ድምጹን እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።
በምስራቅ ሸዋ ዞን በአዳሚ ቱሉ ጂዶ ኮምቦልቻ እና በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ (አሙሩ፣ ጉዱሩ፣ ጂማ ራሬ እና ሆሮ ቡሉቅ) ወረዳዎች በተደረጉ ቅስቀሳዎች፣ ፓርቲው ከፋፋይ የትላንት ትርክትን በወል አገራዊ ትርክት በመተካት የሁሉንም ኢትዮጵያውያን እኩልነትና እውነተኛ ፌዴራሊዝምን ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑ በስፋት ተገልጿል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በምዕራብ ሸዋ ዞን የሚገኙ ወጣቶች፣ የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶችን ተጠቃሚነት በተግባር እያረጋገጠ ያለ የዛሬና የነገው ትውልድ ተስፋ መሆኑን በመጥቀስ፣ ብልፅግናን ለመምረጥ ያላቸውን ዝግጁነት ገልፀዋል።
በተመሳሳይ መልኩ በሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ እና ጫንጮ ከተማ አስተዳደር በተካሄደው ንቅናቄ፣ ፓርቲው ያለፉትን ስህተቶች እያረመና መልካም ተሞክሮዎችን እያሰፋ ለትውልድ የሚተርፍ አገር የመገንባት ራዕይ ይዞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተመላክቷል።
በአጠቃላይ በየዞኖቹ የተካሄዱት እነዚህ የቅስቀሳ መርሃ-ግብሮች፣ ብልፅግና የኢትዮጵያን አንድነት በጽኑ መሰረት ላይ ለመገንባትና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለውን ቁርጠኝነት ዳግም ያሳዩበት እንዲሁም ጠንካራ ማህበራዊ መሰረት ያለዉ ፓርቲ መሆኑ የተሰተዋለበት ንቅናቄ ነበር፡፡
ብልፅግናን ይምረጡ!
ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነዉ!
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!
#prosperity