Prosperity Party

7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ የተጀመረውን የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ወደ ላቀ ምዕራፍ የሚያሸጋግር እንዲሆን ብልፅግና ፓርቲ በቁርጠኝነት እየሰራ ነው- አቶ መለሰ ዓለሙ

የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት ህብረት "ዉጤታማ ምርጫ ለተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል የግማሽ ዓመት ኮንፈረንስ አካሂዷል።

በኮንፈረንሱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በብልፅግና ፓርቲ ዋና /ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ እና የአስተዳደር ክላስተር ሰብሳቢ አቶ መለሰ ዓለሙ፤ ለፉት ስድስት ወራት ዘርፈ ብዙ ዉጤቶች ማሰመዝገብ ያስቻሉ እና ጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ስራን ለማፋጠን የሚያግዙ መለኪያዎች ተዘጋጅተዉ በልዩ ትኩረት ሲሰራ መቆየቱን አስታዉሰዋል፡፡

እንደ ፓርቲ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የያዝነው ዓላማ ግቡን እንዲመታ የአባላት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በየደረጃው ያለዉ አባላችን ባለበት በፈጠራ፤ ፍጥነት እና ዝላይ ቀን ከሌሊት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመጪው ግንቦት ወር የሚካሄደው 7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ በሀገራችን የተጀመረውን የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ወደ ላቀ ምዕራፍ የሚያሸጋግር እንዲሆን ብልፅግና ፓርቲ ቁርጠኛ መሆኑ አስፈላጊዉን ሁሉ ዝግጅት እያከናወነ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ሰላማዊ እንዲሁም በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያለዉ እንዲሆንም የፓርቲው አባላትና አመራሮች የተጣለባቸዉን ድርብ ሀላፊነት በጥብቅ ዲሲፕሊን ሊወጡ እንደሚገባ ገልፀዋል።

በብልፅግና ፓርቲ ዋና /ቤት የስትራቴጂክ ስራ አመራር ዳይሬክተርና የህብረቱ ሰብሳቢ አቶ ተተካ በቀለ በበኩላቸው የዕቅድ ዝግጅት ባህልና ጥራት በከፍተኛ ደረጃ መሻሻሉን፤ የቤተሰብ የውይይት መድረኮች ጥራትና ቀጣይነት እንዲሁም ችግር ፈቺ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች በመስጠት ረገድ ጥንካሬዎች መመዝገባቸውን አንስተዉ፤ ባለፉት ስድስት ወራት የታዩ ጥንካሬዎችን በማላቅ ዉስንነቶችን ወደ ጥንካሬ በመቀየር የህብረቱን  አባላት ለተጨማሪ ተልዕኮ በማዘጋጀት "በሁሉም ልቆ መገኘት" የሚለውን የህብረቱን መሪ ቃል በተግባር የመመንዘር ስራዎች እንደሚሰሩም ገልፀዋል፡፡

በኮንፈረንሱ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ዋና /ቤት ህብረት እና የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚቴ ስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርቶች ቀርበዉ ዝርዝር ዉይይት የተደረገባቸው ሲሆን፤ የቀሪዉን መንፈቅ የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party