Prosperity Party

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዋና ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አደም ፋራህ መልእክት

የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ የውይይት መድረካችንን በስኬት አጠናቀናል።

በዚህ መድረክ የአፈጻጸም ውጤቶቻችንን በጥልቀት ገምግመናል፤ በቀጣይም የሕዝባችንን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጠናል።

ለ3 ቀናት የተካሄደው መድረክ ዓላማውን ባሳካ፣ እጅግ ባማረና በደመቀ ሁኔታ እንዲካሄድ የማዘጋጀት ሚናውን በሚገባ ለተወጣው የአዲስ አበባ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

ቀጣዩ የበጀት ዓመት የጋራ መግባባት የፈጠርንበትን ዕቅድ መሠረት በማድረግ፣ ከምርጫ ማግስት ለሕዝባችን የገባነውን ቃል በተግባር የምናረጋግጥበትና ደማቅ ብልፅግናዊ አሻራችንን በሁሉም መስኮች የምናሳርፍበት እንዲሆን ለአመራራችንና ለአባላቶቻችን ከአደራ ጭምር ማሳሰብ እወዳለሁ!

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party