Prosperity Party

የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ በሶማሊ ክልል በተለያዩ ዞኖች በድምቀት ቀጥሏል

የብልጽግና ፓርቲ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ መነሻ በማድረግ "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!" በሚል መሪ ቃል በሶማሊ ክልል የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች እያካሄደ ያለው የምርጫ ቅስቀሳ በከፍተኛ መነሳሳት ቀጥሎ ውሏል።

በአዋሬ ፣ ጉነገዶ ፣ ወረዳ ጀረር ዞን፣ በገላዲን እና ቦኽ ወረዳ ዶሎ ዞን ፣በሺላቦ ወረዳ ቆረሀይ ዞን ፣ በሰገግ ወረዳ ኖጎብ ዞን ፣ በቀዳዱማ ወረዳ ዳዋ ዞን፣ በደምበል፣ አፍደም ፣ ሚኤሳ ወረዳ ሲቲ ዞን እና በሸቤሌ ዞን የፓርቲው ደጋፊዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት ደማቅ የቅስቀሳ መርሃ ግብሮች ተካሂደዋል።

ለተሻለ ነገ — የብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ!
የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት የስንዴ ነዶ ነው።

#prosperity

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party