Prosperity Party

የብልጽግና ፓርቲ የምረጡኝ ቅስቀሳ በምዕራብ ሸዋ ዞን አቡና ግንደበረት ወረዳ በልዩ ድምቀት ተካሄደ

የብልጽግና ፓርቲ የምረጡኝ ቅስቀሳ በምዕራብ ሸዋ ዞን አቡና ግንደበረት ወረዳ በልዩ ድምቀት ተካሂዷል። በዕለቱም የፓርቲው ደጋፊዎች አደባባይ በመውጣት ለፓርቲው ያላቸውን ጽኑ ድጋፍና ታማኝነት ገልጸዋል።

በመረሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አወሉ አብዲ፤ የብልጽግና ፓርቲን ታላላቅ ስኬቶችና ቀጣይ ግቦችን በዝርዝር አብራርተዋል። አቶ አወሉ በንግግራቸ ብልጽግና ፓርቲ ከተመሰረተባቸው ጥቂት ዓመታት ወዲህ በሀገሪቱ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ምሰሶዎች ላይ ተጨባጭ ለውጦችን አምጥቷል። በተለይም በግብርናው ዘርፍ ምርታማነትን በዕጥፍ ለማሳደግ የተነደፉት እንደ ‘ሌማት ትሩፋት’ ያሉ ስኬታማ ኢኒሼቲቮች፣ የኢትዮጵያን የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት ከመደጎም ባለፈ በምግብ ራሷን እንድትችል እያደረጓት ይገኛሉ፤" ብለዋል።

ምክትል ፕሬዝዳንቱ አክለውም የብልጽግና ግብ ዘላቂ ሰላም የሰፈነባት፣ በቴክኖሎጂ የዘመነችና ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን መገንባት መሆኑን ገልጸዋል። አሁን እየተመዘገቡ ያሉ ሀገራዊ ድሎችን በማስቀጠል፣ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ማሻሻልና ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ማድረግ የፓርቲው የማይናወጥ ራዕይ መሆኑን በአፅንኦት ተናግረዋል።

የምዕራብ ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዲዳ ጉዳታ በበኩላቸው፤ ብልጽግና ከህዝብ የወጣና የህዝብን መሰረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስ በትጋት እየሰራ ያለ ፓርቲ መሆኑን ገልጸው፣ በዞኑም ባለፉት ዓመታት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በመፍታት ረገድ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

ብልፅግናን ይምረጡ!
ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው

#prosperity

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party