የቄለም ወለጋ ዞን ነዋሪዎች የደምቢ ዶሎ ከተማ በተካሄደው የይምርጡኝ ቅስቀሳ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ለብልፅግና ፓርቲ ያላቸውን ድጋፍ በተግባር አሳይተዋል
በቄለም ወለጋ ዞን የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ የቅስቀሳ መርሃ ግብር ተካሂዷል።ብልፅግና እውነተኛ ብዝሃነት የተረጋገጠባትንና የወንድማማችነት እሴት የዳበረባትን ሀገር እውን በማድረግ፣ አካታች የፖለቲካ ባህልና የወል ትርክት በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲበቅል አድርጓል። በሀገራችንን ዉስጥ ስር የሰደደዉን እርስ በርስ የመጠላለፍ እና አግላይነት የሰፈነበትን የፖለቲካ ባህል በመለወጥ፣ ሁሉም ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ወሳኝ ሚና እንዲኖራቸውና ከማግለል ወደ ዉሳኔ ሰጪነት እንዲሸጋገሩ ማድረግ ታሪክ የቀየረ ፓርቲ ነዉ።
ሀገራችን በብልፅግና መሪነት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ በአፍሪካ የሁለንተናዊ እድገት አርአያ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ አዲስ ኃይል በመሆን የሚገባትን ቦታ የምትይዝ ይሆናል።
ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ!
ብልፅግናን መምረጥ ሀገራዊ መግባባት እንዲሰፍን፣ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ እና ሀገራዊ አንድነት እንዲጠነክር መፍቀድ ነው!
ብልፅግናን ይምረጡ!
ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነዉ!
ወደ ተምሳሌት ሀገር ከብልፅግና ጋር!