Prosperity Party

የስንዴ ነዶ፡- የመደመር፣ የአንድነትና የትብብር ተምሳሌት

የስንዴ ነዶ፡- የመደመር፣ የአንድነትና የትብብር ተምሳሌት ነዉ፡፡ የስንዴ ዘንጎች በአንድነት ተሰብስበዉ በገመድ ሲታሰሩ የስንዴ ነዶ ይባላል፡፡ ይህም በነጠላ ካላቸዉ አቅም ይልቅ በህብረት የሚፈጥሩትን ጥንካሬና ዉጤት ያሳያል፡፡ ፓርቲያችን የመደመር ፓርቲ አቃፊ አካታችና ህብረብሄራዊ ሀገራዊ ፓርቲ ነዉ፡፡
ኢትዮጵያዊያንን ሁሉ ከዳር እስከ ዳር አሰባስቧል፡፡ ፓርቲያችን በራሱ የህብረብሄራዊ አንድነት ተምሳሌት ነዉ፡፡ ይህ የመደመር፣ የአንድነትና የትብብር ትርክት የኢትዮጵያዊያን ትርክት ሆኗል፡፡ በዚህ ትርክት ኢትዮጵያዊያን በብሄር፣ በሀይማኖት፣ በቋንቋ፣ በባህል ሳይከፋፈሉ በብዛነት ዉስጥ ለደመቀችዉ ህብረብሄራዊት ኢትዮጵያ በአንድነት በጋራ እንዲሰባሰቡ በር ከፍቷል፡፡
በቀጣዮቹ ዓመታት ፓርቲያችን ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን የመደመር፣ የአንድነትና የትብብር ተምሳሌት በመሆን የምርጫ ምልክታችን ሆኖ ቀርቧል፡፡ እኛ የመደመር ፓርቲ ነን፡፡ እደ ስንዴ ዘንጎች በነጠላ ከመቆም ይልቅ በህብረት ታስረን የጸናን የነዶ ጥንካሬዎች፡፡

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party