Prosperity Party

የስንዴ ነዶን መምረጥ የብልጽግናንና የሉዓላዊነትን ጉዞ ማጽናት ነዉ

በድሬዳዋ አስተዳደር ወረዳ ሁለት፣ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች ተካሂዷል።

በዚሁ መርሃ-ግብር ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገበየሁ ጥላሁን፤ “የስንዴ ነዶ የኢትዮጵያ የራስን በራስ የመመገብ ህልም የታተመበት፣ የልፋታችን ውጤት እና የብልጽግናችን ማረጋገጫ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
ብልፅግና ፓርቲ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ የሀገርን ሉዓላዊነት በጠንካራ ኢኮኖሚ ላይ ለመገንባት ሌት ተቀን እየሰራ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ ገበየሁ፤ በተለይም በግብርናው ዘርፍ የተመዘገቡ አመርቂ ውጤቶች ኢትዮጵያን ከስንዴ ልመና ያወጡና የምግብ ዋስትናዋን በተግባር ያረጋገጡ ታላላቅ ድሎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
አያይዘውም "የስንዴ ነዶን መምረጥ የብልጽግናንና የሉዓላዊነትን ጉዞ ማጽናት ነው" ብለዋል።
የወረዳ ሁለት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አቤል ምስራቅ በበኩላቸው፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች፣ የወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የሰላም ግንባታ ሥራዎች፤ ብልፅግና ፓርቲ ለሕዝቡ የገባውን ቃል በተግባር እየፈጸመ መሆኑን የሚያሳዩ ማሳያዎች መሆናቸውን አመላክተዋል።
የተጀመሩ የልማት እና የዴሞክራሲ ግንባታ ሥራዎችን ለማስቀጠል፣ ብሎም ለቀጣዩ ትውልድ የምትሆን የተከበረች ሀገር ለማቆየት፤ የአንድነት እና የብልፅግና ምልክት የሆነውን 'የስንዴ ነዶ'ን መምረጥ እንደሚገባ በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተሳተፉ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ገልጸዋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party