የሴቶች ቀን ሲከበር በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ሴቶች ለአለም ያበረከቱት አስተዋጽኦ የሚታወስበት በዓል ነው - የብልፅግና ፓርቲ የዲጂታል ሚዲያ ሚኒስትር ድኤታ ፈዲላ ቢያ
አለማቀፍ የሴቶች ቀን "50 አመት የሴቶች ድምፅ ለእኩልነትና የበለፀገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ሴት ምሁራን በተሳተፉበት የውይይት መድረክ በድሬዳዋ አስተዳደር ተከብሯል።
በመድረኩ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ህዝብና አለም ዓቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ፈዲላ ቢያ እንደገለጹት ማርች 8 ሴቶች በኢኮኖሚው፣ በሳይንስ እና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ እውቀትን፣ ክህሎትን አዳዲስ ግኝቶችን ለአለም በተግባር ያሳዩበትን ቀን የሚታወስበት ነው።
የሀገራችን ሴቶች የአሁኑን ትውልድ እውቀት በመቅረፅ እና የቀጣይ ትውለድን ራዕይ በማመላከት ፋና ወጊ መሆናቸውን በንግግራቸው ጠቁመዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከፍተኛ ትምህርት ተቋሟት ሴቶች ወደ መሪነት እንዲመጡ በማብቃት ረገድ ምቹ መደላድል ሊፈጥሩ እንደሚገባ ተናግረዋል።
ሴቶች ሰላምን በማፅናቱ ስራ ያላቸውን ከፍተኛ ሚና በቁርጠኝነት ለማስቀጠል የድሬ ዳዋ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ባሰናዳው አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ዝግጅት ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ወ/ሮ ከሪማ አሊ፣ የአስተዳደሩ ከንቲባ ተወካይ ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ እና ከተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተገኙ ሴት ምሁራን ተሳትፈዋል።