የመደመር መንግሥት ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ጠንካራ ተቋማትን በመገንባት፣ ብቃት ባለው አፈጻጸም፣ በትብብር፣ በሥርዓት ግንባታና ከፍተኛ ሀገራዊ ራእይ ላይ የተመሠረተ ነው- የመደመር መንግስት
የመደመር አንቀፅ
"የፖለቲካ ንግድ አስተሳሰብ ትኩረቱ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ሀብትና የፖለቲካ ኃይልን መቀራመት እንደመሆኑ፣ ፈጠራንና ፍጥነትን ትኩረት ላደረገው ለመደመር መንግሥት ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ግንባታ ዋና ደንቃራ ነው።
የመደመር መንግሥት ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ጠንካራ ተቋማትን በመገንባት፣ ብቃት ባለው አፈጻጸም፣ በትብብር፣ በሥርዓት ግንባታና ከፍተኛ ሀገራዊ ራእይ ላይ የተመሠረተ ነው።
የሐሳብ አልባ የፖለቲካ ምኅዳር ግን ሕጋዊና ተቋማዊ ባልሆነ የጥቅም ትሥሥር፣ በሽኩቻ፣ በግላዊና በቡድናዊ ፍላጎት ላይ ይመሠረታል።ሀብት ፈጠራ እንዲካብትና ፖለቲካዊ ኢኮኖሚው እንዲረጋጋ፣ ጠንካራ ተቋማት ያሉት እና ፖለቲካዊ ስምምነትና ቁርጠኝነት ያለው ልሂቅ ሊኖር ይገባል።"
የመደመር መንግሥት - ገፅ 312