ዛሬ በመላው አፍሪካ እና ጥቁር ሕዝብ ላይ ጨልሞ በነበረ ሰማይ ፀሐይ የፈነጠቀበት ቀን ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ዛሬ በመላው አፍሪካ እና ጥቁር ሕዝብ ላይ ጨልሞ በነበረ ሰማይ ፀሐይ የፈነጠቀበት ቀን መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ድንበሯን ገፍቶ ሉዐላዊነቷን እና የሕዝቧን ነጻነት የደፈረውን የወራሪውን ጦር በዓድዋ ተራሮች ድል የነሳችበት እና ለሶስት ሺህ ዓመታት ያልተደፈረውን ስልጣኔዋን ያጸናችበት ቀን መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡
ተከብረን የምንኖርባትን ኢትዮጵያን ከድንቅ ስልጣኔ እና ታሪክ ጋር ከነታላቅ ክብሯ በደም መስዋዕትነት ላስረከቡን አባቶቻችን ክብር ይገባቸዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዛሬ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አባቶችና እናቶች ሞተው ያቆሟትን ሀገር በአንድነት እና በፍቅር በመኖር ሊያስቀጥሉ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
ከእነሱ በመማር ድህነትን፣ መከፋፍልን፣ እና ኋላ ቀር አስተሳሰብን አሻፈረኝ በማለት ኢትዮጵያን ወደ ብልፅግና ልናሻግር ይገባል ያሉት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፤ ኢትዮጵያ ከሆነችው በላይ ታላቅ የምትሆንበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆንም ገልጸዋል።
#Adwa130 #PMAbiy #Ethiopia