ወጣቱ ብልፅግናን በመምረጥና በማስመረጥ ሀገር የማፅናትና የተጀመሩ ስራዎችን የማስቀጠል ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል!
#ኢትዮጵያን_ወደ_ተምሳሌት ሀገር
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ አባላትና ደጋፊዎች በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ዞኖች ደማቅ የምርጫ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ አድርገዋል።
በተካሄዱት የድጋፍ ሰልፎች በ 7ተኛው ዙር ጠቅላላ ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ ወጣቱ ብልፅግናን በመምረጥና በማስመረጥ ሀገር የማፅናትና የተጀመሩ ስራዎችን የማስቀጠል ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።
ብልፅግና ፓርቲ የትውልድና የወጣት ፓርቲ መሆኑ በሰልፎቹ የተመላከተ ሲሆን ባለፉት ዓመታት በፓርቲው መሪነት ለበርካታ ወጣቶች ጊዚያዊና ቋሚ የስራ ዕድል መፍጠር እንደተቻለ ተመልክቷል።
ወጣቱ የብልፅግና ዕሳቤን በመያዝ አሰባሳቢ ገዢ ትርክትን የመገንባት፣ የሀገር አንድነትን የማፅናት፣ እንዲሁም የኢትዮጵያን ሰላም የማስጠበቅ ሚናዉን እንዲወጣ ተጠይቋል።
ወጣቱ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧት ጀምሮ በነቂስ በመውጣት የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት የሆነውን የስንዴ ነዶን በመምረጥ ሀገርን እንዲያስቀጥሉና እንዲያፀኑ ጥሪ ቀርቧል።
ብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም በድጋፍ ሰልፎቹ ተጠቁሟል።
7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ወጣቱ ከፀጥታው አካላት ጋር በመቀናጀት የበኩሉን ድርሻውን እንዲወጣም ተጠይቋል።
ወጣቶች በ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት መሳተፍ ብቻ ሳይሆን ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ጠንካራ ሚና በመጫወት ግንቦት 24 በአደረጃጀታቸዉ በመወጣት ድምፅ መስጠት አለባቸው ተብሏል።
በክልሉ ካለው አመራር ከ64 በመቶ በላይ ወጣቶች መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ይህም ወጣቱ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታ በመሆን ሀገር የመምራት ሚናዉን እንዲወጣ በብልፅግና ፓርቲ የተወሰደ አቋም መሆኑ ተጠቅሷል።
ብልፅግናን መምረጥ ሀገርን ማፅናት፣ ማልማት፣ ማስቀጠልና ማሳደግ በመሆኑ በመጪው ሀገራዊ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ ምርጫ ምልክት የሆነውን ስንዴ ነዶን ወጣቱ እንዲመርጥ ጥሪ ቀርቧል።
#prosperity