Prosperity Party

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማት እና የኃይል ሽግግር ያላትን የላቀ ሚና አጠናክራ ትቀጥላለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማት እና የኃይል ሽግግር ያላትን የላቀ ሚና መጫወቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እና በፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በጋራ አዘጋጅነት በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው የአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባኤ የኢትዮጵያን ተሞክሮ ማካፈላቸውን ገልጸዋል።
በተለይም የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማት እና የኃይል ሽግግርን በተመለከተው ውይይት መድረክ ላይ ከኢትዮጵያ ተሞክሮ የተቀዱ ከፍ ያሉ ሀሳቦች መነሳታቸውን አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ በተነሱት ሁለት ዘርፎች የጀመረችውን ስራ በማጠናከር የላቀ ሚና መጫወቷን እንደምትቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party