Prosperity Party

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር በሚል መሪ ቃል የምርጫ ቅስቀሳና ቡና ጠጡ ፕሮግራም ተካሄደ

በካፋ ዞን ጠሎ ወረዳ ጉታ ቀበሌ በሴቶች ክንፍ አስተባባሪነት የምርጫ ቅስቀሳና ቡና ጠጡ ፕሮግራም ተካሂዷል።

በቡና ጠጡ ፕሮግራም ሴቶች በ7ተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲን እንዲመርጡ ግንዛቤ መስጠት ተችሏል።

በምርጫው የብልጽግና ፓርቲ ምልክት የስንዴ ነዶ በመሆኑ የስንዴ ነዶ እንዲመርጡ የተገጸ ሲሆን ፕሮግራሙ በሁሉም ቀበሌዎች እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።

በፕሮግራሙ ላይ የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ አልማዝ ብርሃኑ፣ የሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ቅድስት አበበ እና በፈለገ-ሠላም ምርጫ ክልል የክልል ምክርቤት እጩ ተወካይ ወ/ሮ ሸዋይ አግደውን ጨምሮ የክንፉ አመራሮችና አባላት ተገኝተዋል።

#Prosperity

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party