አራዳ ፓርክ
ይህ በአዲስ አበባ እምብርት የሚገኝ የከተማ ውስጥ ድንቅ የሕዝብ መገልገያ ማዕከል ሲሆን በሁሉም እድሜ እና ማኅበራዊ ሁኔታ ያሉ ሰዎች በጋራ የሚሰበሰቡበት፣ የሚዝናኑበት፣ ጽዱ እና ደማቅ አድርገው በመጠበቅም የሚኮሩበት ስፍራ ነው። 40 ሄክታር ላይ ካረፈው ፓርክ 15 ሄክታሩ በለምለም አረንጓዴ መስክ የተሰናዳ ሲሆን 6 ኪሎሜትር የእግረኛ መንገድ፣ 5 ኪሎሜትር የብስክሌትና መሮጫ ትራክ የተዘጋጀለትም ነው። ይህም ንቁ እና ጤናማ አኗኗርን የሚያበረታታ ነው። በፓርኩ 131 ሱቆች፣ ካፌዎች፣ የአገልግሎት መስጫዎች፣ የስፖርት እና የባሕል እና ጥበባት መከወኛዎች፣ እንደየሕፃናት መጫወቻ እና አነስተኛ የሕፃናት ከተማ ያሉ የቤተሰብ መዝናኛዎች ይገኛሉ። እነዚህ ሁሉ በቁመቱ በሀገራችን ቀዳሚ በሆነው ግዙፍ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ሥር ሲታዩ ደግሞ የኅብረት እና የጋራ ኃላፊነት ተምሳሌትነቱን ያጎሉታል።