ተደምረን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊ እና ተዓማኒ እንዲሆን ማድረግ ይገባናል - ወጣት ፈዲላ ቢያ
የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ዋና ጽ/ቤት ከፌደራል ተቋማት ብልጽግና ወጣቶች ክንፍ ጋር በመሆን የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ማኒፌስቶና መወዳደሪያ ምልክት ማስተዋወቂያ ፕሮግራም በ4 ኪሎ ፕላዛ አካሄደ።
በመድረኩ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲው የወጣቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዝዳት እና የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ህዝብ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስትር ዴኤታ ወጣት ፈዲላ ቢያ እንደገለፁት እኛ ወጣቶች ተደምረን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊ እና ተዓማኒ እንዲሆን ማድረግ ይገባናል።
ብልፅግና ፓርቲ ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ ወጣቱን አሳታፊ ያደረጉ ሰፋፊ ስራዎችን በመስራት ፓርቲው የትውልድ ፓርቲ መሆኑን አስመስክሯል ብለዋል።
ፓርቲያችን የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ በማሳደግ ረገድ ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል ።
ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፓርቲው አባል የሆኑ ወጣቶች የነቃ ተሳትፎ በማድረግ አርአያ ሊሆኑ እንደሚገባም አሳስበዋል።