Prosperity Party

ቮይስ ኦፍ ፕሮስፐሪቲ መፅሄት 2ኛ እትም ወደ አንባቢያን ሊደርስ ነው!


የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ የሚያዘጋጀው "Voice of Prosperity" መፅሄት ሁለተኛ እትም (Vol. 1 No. 2) በቅርቡ ለንባብ ይበቃል።

በዚህ በጉጉት እየተጠበቀ በሚገኘዉ እትም የሚዳሰሱ ዋና ዋና ጉዳዮች፡-

°የ7ኛው አገራዊ ምርጫ ታሪካዊ ስኬቶች፦ ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች የተሳተፉበት እና የኢትዮጵያን የዲሞክራሲ ምህዳር በከፍተኛ ሁኔታ ያሰፋው ታሪካዊ ምርጫ አጠቃላይ እይታ፣ ትንታኔና የተወሰዱ ጠቃሚ ልምዶች።

°ልዩ ቃለ-መጠይቅ፦ ከፓርቲው ዋና ፅ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ክቡር ዶ/ር ሰማ ጥሩነህ ጋር የተደረገ ቆይታ፤ በመደመር ፍልስፍና ላይ የተመሰረተው የድህረ-ምርጫ የሰላምና የዲሞክራሲ ግንባታ ሥርዓት፣ የአማራጭ ድምፆች በመንግስት አስተዳደር ውስጥ መካተት እንዲሁም የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን (ENDC) የእስካሁን ስኬቶች ተብራርተዋል።

° የኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን ስኬቶች፦ በ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ አማካኝነት የአምራች ኢንዱስትሪው አቅም ከ46% ወደ 66.3% ማደግ፣ ባለፉት 9 ወራት ውስጥ ከዉጭ የሚገቡ ምርቶችን በሃገር ዉስጥ በማምረት 4.85 ቢሊዮን ዶላር ማዳን መቻሉ እና አዳዲሶቹ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክና የሞጆ ሴራሚክ ፋብሪካ የስራ አፈፃፀም ማሳያዎችን የሚዳስሱ ፅሁፎች ተካተዋል።

° የመደመር ፍልስፍና፦ የ"መደመር" ፍልስፍና ለሀገራዊ አንድነት፣ ለሁለንተናዊ ብልፅግና እንዲሁም ለአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ትስስር እያበረከተ ያለው ሚና በዝርዝር ተተንትኗል።

 ይህንን ልዩ እትም ወዲያውኑ ለማግኘት የፓርቲያችንን ድረ-ገጽ (www.prosperity.org.et) እንዲሁም ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችንን ይከታተሉ!

#ብልፅግና_ፓርቲ #VoiceOfProsperity #VOP #መደመር

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party