Prosperity Party

ብልፅግና ፓርቲ በመተባበርና በመተጋገዝ የአካታችን ፖለቲካ ሥርዓትን በማጠናከር ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር ሀገራዊ ስኬቶችን እያስመዘገበ ይገኛል ፡- አቶ ማስረሻ በላቸው

 

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የግብርና ቢሮ ኃላፊና እንዲሁም በ7ኛ ዙር ሀገራዊ ምርጫ በቢጣ ጌሻ ምርጫ ክልል፣ በክልል ምክር ቤት ዕጩ አቶ ማስረሻ በላቸው ብልፅግና በሀገር ደረጃ፣ ከክልል እስከ አካባቢ ዘርፈ ብዙ ትሩፉቶችን ማስመዝገቡን ተናግረዋል።

አቶ ማስረሻ አክለው  ብልፅግና ፓርቲ የካፋ ህዝብን ባህሉንና ታሪኩን ጠብቆ ከወንድም ህዝቦች ጋር ክልል መሥርቶ በቅርበት አገልግሎት እንዲያገኙ ያስቸለ መሆኑን ለተሳታፊዎች ገልፀዋል።

ብልፅግና በመተባበርና በመተጋገዝ  የአካታችን ፖለቲካ ሥርዓቶችን በማጠናከር ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር ሀገራዊ ስኬቶችን እያስመዘገበ መሆኑን  ገልፀዋል አቶ ማስረሻ።

በሀገር ደረጃ ያስጀርናቸውን የለውጥ ጉዞዎችን ከግብ ለማድረስ ኩሩ የጌሻ እና ደካ ማህበረሰቦችን ዛሬ ያሳዩትን አለኝታ በግንቦት 24/2018ዓ/ም እንዲያረጋግጥ ጠይቀዋል።

ብልፅግና ፓርቲ ሀገር እየገነባ መሆኑን የገለፁት ደግሞ በትውውቅ መረኃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት በክልል ምክር ቤት ዕጩ እና የካፋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ  አቶ አጥናፉ ኃይሌ የሀገር ግንባታውን ከግብ ለማድረስ ህዝባችን ተሳትፎና ድጋፍ ያስፈልገናል ብለዋል።

ብልፅግናን ስንመርጥ  ለምርጫ መረኃ ግብር ሳይሆን ተምሳሌት የሆነችውን ኢትዮጵያ ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ መሆኑን አቶ አጥናፉ አስገንዝበዋል።

የለውጥ ትሩፉት ወደ ሆነችሁ ደካ ከተማ አስተዳደር በእንኳን መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የደካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አድነው ኃይሌ ከተማችን ለውጥ ትሩፋቶችን እየተቋደሰች ትገኛለች ብለዋል።

በፓርቲ መሪነት የተጀመሩ የህዝቦቻችን የመልማትና የመልካም ጥያቄዎችን ከግብ እንዲደርሱ መላው ማህበረሰባችን ድጋፉን በምርጫም እንዲያስመሰክር ጠይቋል።

#prosperity

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party