ብልጽግና ፓርቲ "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እያካሄደ ያለው የምረጡኝ ዘመቻ በምስራቅ ባሌ ዞን፣ በቢሾፍቱና ባቱ ከተሞች በታላቅ ህዝባዊ ንቅናቄ ቀጥሏል
ብልጽግና ፓርቲ "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እያካሄደ ያለው የምረጡኝ ዘመቻ በምስራቅ ባሌ ዞን፣ በቢሾፍቱና ባቱ ከተሞች በታላቅ ህዝባዊ ንቅናቄ ቀጥሏል።
በምስራቅ ባሌ ዞን በተካሄደው ልዩ የምረጡኝ ዘመቻ ላይ የብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ የፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር መንግስቱ በቀለ ለታዳሚዎች ባስተላለፉት መልዕክት ብልጽግና ፓርቲ በሁሉም ዘርፎች ስኬቶችን በማስመዝገብ የሀገሪቱን የሽግግር ጉዞ እያሳካ ይገኛል። በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የተጀመረው ለውጥ በፅኑ መሰረት ላይ እንዲቆም እና ኢትዮጵያ የብልጽግና ተምሳሌት ሆና እንድትገነባ ፓርቲያችን ሌት ተቀን ይሰራል። ምርጫችሁ ብልጽግና ሲሆን፣ እናንተ የምትመርጡት ጊዜያዊ መፍትሄን ሳይሆን ለልጅ ልጆቻችሁ የምትተርፍ የበለፀገችና የተከበረች ሀገርን ነው።" ብለዋል
በተመሳሳይ በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደው ንቅናቄ፣ ነዋሪዎች ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተገኙ ድሎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል። ፓርቲው የዜጎችን ህይወት ለማሻሻልና ዜጎች በሀገራቸው በክብር የሚኖሩባትን ሁኔታ ለመፍጠር የሚሰራ በመሆኑ "ምርጫችን ብልጽግና ነው" ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተዋል።
በባቱ ከተማ አስተዳደርም የብልጽግና ፓርቲ የምረጡኝ ዘመቻ በከፍተኛ ድምቀት ተካሂዷል። በንቅናቄው ላይ የታደሙት ነዋሪዎች ለፓርቲው ያላቸውን ደጋፊ ገልፀዋል። ብልጽግና ሀገራችንን ካለችበት ሁለንተናዊ ስብራት በማውጣት ወደ ታላቅነት እያሸጋገራት እንደሚገኝ በዕለቱ ተገልጿል። ፓርቲው ባሳየው ጠንካራ አመራርም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት ተቀባይነትና ተሰሚነት እየጨመረ መምጣቱ ተመላክቷል።
በእነዚህ ሶስት አካባቢዎች የታየው ከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎና ድጋፍ ብልጽግና ፓርቲ ለኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋ ይዞ መነሳቱን የሚያሳይ መሆኑን ያመላከተ ነዉ።
ብልፅግናን ይምረጡ!
ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነዉ!
#prosperity