ብልጽግና ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች እና ዞኖች ደማቅ የምርጫ ቅስቀሳ አካሄደ
ብልጽግና ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል አዳማ እና ነጆ ከተማ እንዲሁም በምስራቅ ወለጋ ዞን ጎቡ ሰዮ ወረዳ "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌታዊት ሀገር!" በሚል መሪ ቃል ሰፊዉን የማህበረሰብ ክፍል ያሳተፈ ደማቅ የምርጫ ቅስቀሳ አካሂዷል፡፡
በአዳማ ከተማ በዳቤ እና ሉጎ ክፍለ ከተሞች በተካሄደው በዚህ የምረጡኝ ቅስቀሳ መርሃ-ግብር ላይ የፓርቲው ደጋፊዎችና የከተማዋ ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተዉ የተገኙባቸ ሲሆን፣ ፓርቲው ሁሉን አቀፍ እና ብዝሃነትን ያከበረ ስርዓት በመገንባት ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የብልጽግና ምዕራፍ ለማሸጋገር የጀመረውን ጉዞ ለማስቀጠል ህዝቡ ድምፁን እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።
በነጆ ከተማ አስተዳደርና ምስራቅ ወለጋ ዞን ጎቡ ሰዮ ወረዳ በተካሄደዉ ሰልፍ፤ ብልጽግና ፓርቲ የሀገርን ሉአላዊነት በሁሉም ዘርፍ እያስከበረ፣ ኢኮኖሚያችን እንዲያድግ የሚያስችሉ ስትራቴጂዎችን ቀርጾ በትጋት እየሰራ በመሆኑ፤ "ምርጫችን ብልጽግና ፓርቲ ነው" ሲሉ የወረዳው ነዋሪዎች ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።
የዞን እና የከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ እስከ ገጠር ድረስ የዘለቀዉ የምርጫ ቅስቀሳ ስራ በከፍተኛ መነሳሳት እየተካሄደ እንደሆነና በሁሉም ቦታዎች ሰፊ የምርጫ ቅስቀሳ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገልፃል። ብልጽግና ፓርቲ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች መብትና እኩልነት የተከበረባትን ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት ያለውን ራዕይ እንዲሁም ሌሎች ሰፋፊ አጀንዳዎቹን በየደረጃው ለሚገኘው የማህበረሰብ ክፍል እያስተዋወቀ ይገኛል። ለተሟላ ሰላም፣ለዜጎች እኩልነትና ቀጣይነት ላለዉ ሁለንተናዊ ልማት ብልጽግና ፓርቲ ብቸኛው አማራጭ ነዉ።
ብልፅግና ፓርቲ ኢትዮጲያን ወደ ተምሳሌታዊት ሀገርነት የመቀየርና የኢኮኖሚ ነፃነትን የማረጋገጥ ዓላማውን በህዝብ ድጋፍ ለማፅናት በቆራጥነት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
ለተሻለ ነገ — የብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ!
የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት የስንዴ ነዶ ነው።