Prosperity Party

ብልጽግና ፓርቲ በመደመር እሳቤ የኢትዮጵያን እድገትና ከፍታ የማስቀጠል ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ ገለፁ

በጋምቤላ ክልል "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ሐሳብ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መርሐ-ግብር ተካሂዷል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ እንዳሉት ብልጽግና ፓርቲ በመደመር እሳቤ የኢትዮጵያን እድገትና ማንሰራራት የማስቀጠል ተግባሩን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በፓርቲው አመራር ሰጪነት ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች እድገት እያስመዘገበች መሆኑን ጠቁመው በቀጣይም ለላቀ ውጤት እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

ፓርቲው የበለፀገች ሀገር ለትውልድ ለማስረከብ የጀመረውን ሁለንተናዊ ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ርዕሰ መስተዳድሯ ተናግረዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የጋምቤላ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሽኔ አስቲን በበኩላቸው ብልፅግና ፓርቲ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ሲያከናውን እንደቆየ ተናግረዋል።

በባለፉት የለውጥ ዓመታት የሀገርን እድገትና የህዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን በመተግበር ተጨባጭ ውጤቶች ማስመዝገቡንም አስታዉሰዋል።

ኢትዮጵያን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ የጀመራቸውን ተግባራት አጠናክሮ እንዲያስቀጥል ህዝቡ ከፓርቲው ጎን ሊቆም እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል።

የጋምቤላ ከተማ ዋና ከንቲባ አቶ ቱት ጆክ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ዘርፎች በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ጠቁመዋል።

በቅስቀሳ መርሐ-ግብሩ ላይ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ጋትሉዋክ ሮን እና ሌሎች ብልጽግና ፓርቲን በመወከል ለክልል ምክር ቤት የሚወዳደሩ እጩዎች እንዲሁም የፓርቲው አባላት እና ደጋፊዎች ተገኝተዋል።

#Prosperity

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party