ብልጽግና ፓርቲ ለሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ
በድሬዳዋ አስተዳደር በሴቶች የተዘጋጀ የብልፅግና ፓርቲ የአደባባይ የምርጫ ቅስቀሳ ተካሄደ።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት ሴቶች በፖለቲካው ውሳኔ ሰጪነት ላይ ያላቸው ተሳትፎ ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር የተደረገ ሲሆን፣ በኢኮኖሚው ዘርፍም በንግድ፣ በግብርና፣ በአገልግሎትና በፈጠራ ሥራዎች ላይ ተጠቃሚነታቸው እንዲያድግ ሰፊ ሥራዎች መከናወናቸው በመድረኩ ተመላክቷል።
በመርሃ-ግብሩ የድሬደዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ክቡር አብዲ ሙክታር፣ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ፣ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድሬዳዋ ተወካይ ቢፍቱ መሀመድ(ዶ/ር)፣ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ፣የአስተዳደሩ ሴት አመራሮች እንዲሁም የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ተገኝተዋል።
#prosperity