Prosperity Party

ባለፉት አምስት ዓመታት ባልተቋረጠ ሁኔታ በተከናወኑ ተግባራት ሴቶችን የሀገር ብልፅግና ጽኑ መሰረት ማድረግ ተችሏል -ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ባለፉት አምስት ዓመታት ባልተቋረጠ ሁኔታ በተከናወኑ ተግባራት ሴቶችን የሀገር ብልፅግና ጽኑ መሰረት ማድረግ መቻሉን የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባልና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ ይህንን የገለጹት የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ብቻ የተሳተፉበትን የምርጫ ቅስቀሳ ንቅናቄ ባካሄደበት ወቅት ነው።
በዓይነቱ ልዩ በሆነው በዚህ መድረክ ላይ የፓርቲው ዕጩዎች እና ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ደጋፊዎች ተገኝተዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ያለ ሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሀገርን ብልፅግና ማረጋገጥ የማይታሰብ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ባለፉት አምስት ዓመታት በሴቶች ላይ ትኩረት አድርገው የተከናወኑ ስራዎች ትልልቅ ስኬቶች እንዲመዘገቡ አስችለዋል ብለዋል።
ሴቶች በከተማዋ ቁልፍ ተቋማትን በብቃት እየመሩ ይገኛሉ ያሉት ከንቲባዋ ይህም ለተሳትፎ ብቻ ሳይሆን በተግባር ውጤታማነታቸውን ያረጋገጡበት መሆኑ ገልጸዋል።
በስራ ዕድል ፈጠራ ረገድ ሴቶችን በጉልህ ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለባቸው ውጤታማ ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።
የብልፅግና ጉዞ ማንንም ወደ ኋላ የማይተው መሆኑን የጠቆሙት ከንቲባዋ፣ የፓርቲው ፖለቲካ ባዶ ፕሮፓጋንዳ ሳይሆን በተግባር የሚታይ ውጤት መሆኑን አስገንዝበዋል።
ባለፉት ዓመታት በከተማዋ ለሴቶች ተጠቃሚነት የተሰሩ ዓበይት ተግባራት ፓርቲው ለሴቶች የሰጠውን ትልቅ ክብርና ስፍራ የሚያሳዩ መሆናቸውም በመድረኩ ተስተጋብቷል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party