ባለፉት ስምንት ዓመታት የተሰሩ ስራዎች ሀገርና ሕዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ ናቸው - አቶ አደም ፋራህ
ባለፉት ስምንት ዓመታት በሁሉም ዘርፎች የተሰሩ የሪፎርም ስራዎች ሀገርና ሕዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ ናቸው አሉ በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፡፡
የ2018 በጀት ዓመት ሶስተኛው የ100 ቀናት እና የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን÷ መድረኩን ተከትሎ አቶ አደም ፋራህ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በማብራሪያቸውም ባለፉት ዓመታት ከተሰሩ ስራዎች መካካል አንደኛው የፖለቲካ ሪፎርም መሆኑን በማንሳት÷ በዚህም የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት በፓርቲዎች መካከል ያለው የፉክክር እና የትብብር ሚዛን እንዲጠበቅ ተደርጓል ነው ያሉት፡፡
በገዢው ፓርቲ እና ተፎካካሪ ፓርቲዎች መካካል ያለው ግንኙነት ጤናማ እንዲሆንና በብሄራዊ ጥቅሞች ላይ በትብብር መስራት የተቻለበት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ከወረዳ እስካ ፌዴራል ድረስ ከ275 በላይ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች በተለያዩ የመንግስት ኃላፊነቶች ላይ ተመድበው እየሰሩ መሆናቸውንም ለአብነት አንስተዋል፡፡
በሌላ በኩል ለዘመናት ሲንከበላሉ የመጡ ሀገራዊ ችግሮችን ለመፍታት ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞ በስራ ላይ መሆኑን የገለጹት አቶ አደም÷ ይህም የፖለቲካ ሪፎርሙ ሌላኛ መገለጫ ነው ብለዋል፡፡
በኢኮኖሚ ሪፎርም ስራም የወጪ ንግድ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን በመጥቀስ÷ ከውጪ ይገቡ የነበሩ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት አመርቂ ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል፡፡
በአጠቃላይ በማህበራዊ እና በትምህርት ዘርፎች ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡንና በቀጣይም ይበልጥ ሀገራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ብትጋት መስራት እንደሚገባም አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡
#prosperity