በድሬዳዋ አስተዳደር በለውጡ ዓመታት የተሰሩ የልማትና ሰው ተኮር ስራዎች ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነትና ለሕዝቦች አብሮነት መጠናከር ጉልህ አስተዋጽኦ ማድረጋቸው ተገለፀ
ለ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ቀጥሏል፣ በዛሬው ዕለት በመኪና ላይ እና በባህላዊ ውዝዋዜዎች የታጀበ ደማቅ ቅስቀሳ ተከናውኗል።
በመርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወንደሰን አባይ፤ በድሬዳዋ አስተዳደር በለውጡ ዓመታት የተሰሩ የልማትና ሰው ተኮር ሥራዎች ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነትና ለሕዝቦች አብሮነት መጠናከር ጉልህ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን አመላክተዋል።
ድሬዳዋ የሕብረ-ብሔራዊነትና የአብሮነት መፍለቂያ እንደመሆኗ፣ ይህንን እሴት ጠብቆ በማቆየት ከተማዋን ወደ ላቀ ከፍታ ለማውጣትና የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ከግብ ለማድረስ የስንዴ ነዶን መምረጥ እንደሚገባም ተናግረዋል።
ኃላፊው አያይዘውም ፓርቲው ባለፉት ዓመታት የነዋሪውን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ዘመናዊ የገበያ ማዕከላት ግንባታን፣ የመሠረተ-ልማት ማስፋፊያዎችን እና የከተማ ግብርናን በማዘመን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በርካታ ሥራዎችን ማከናወኑን ጠቁመዋል።
እነዚህ ሥራዎች የነዋሪውን ተጠቃሚነት ከማረጋገጣቸው ባለፈ፣ በከተማዋ ያለውን ጠንካራ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር እና አብሮነት ይበልጥ ያጠናከሩ መሆናቸውንም አቶ ወንደሰን ገልጸዋል።
በቅስቀሳው መርሐ-ግብር ላይ የተሳተፉ የፓርቲው አባላት በበኩላቸው፤ ባለፉት ዓመታት የታዩት የመሠረተ-ልማት ዝርጋታዎችና የሰላም ግንባታ ሥራዎች ድሬዳዋን የንግድ ማዕከል ከማድረጋቸው ባለፈ፣ በተለያዩ ብሔረሰቦች መካከል ያለውን የቆየ አብሮነትና ወንድማማችነት ይበልጥ እንዲጸና አድርገዋል ሲሉ ተናግረዋል።
#prosperity