በደሴ ከተማ አስተዳደር በቦርከና፣ ሳላይሽ እና ቢለን ቀበሌዎች የ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት የማስተዋወቅና የምርጫ ቅስቀሳ መርሀ-ግብር ተከናውኗል
በአደባባይ የቅስቀሳ መርሃ ግብር ላይ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት ስለሆነው ''የስንዴ ነዶ'' ትርጓሜና ፋይዳ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
የቅስቀሳ መርሃ ግብሩ ፓርቲው ከማህበራዊ መሰረቶቹ ጋር ያለውን ጥንካሬ ያሳየና በከተማዋ ለሚካሄደው ምርጫ ትልቅ መነቃቃትን የፈጠረ እና ብልጽግና በአብላጫ ድምፅ ለማሸነፍ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የክልል ደጋፊ አመራሮች፣የከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት እና የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና የክልል ም/ቤት እጩ ተወዳዳሪዎች ተገኝተዋል።
ብልፅግና ፓርቲን ይምረጡ!
ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነዉ!
#prosperity