በዛሬው ዕለት በታሪካዊቷ የሻሸመኔ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መርሃ-ግብር በስፖርታዊ እንቅስቃሴ በታላቅ ድምቀት ተጀምሯል
የሻሸመኔ ከተማ እና የምዕራብ አርሲ ዞን ነዋሪዎች በማለዳ ተገኝተው በጋራ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ለፓርቲያቸው ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።
ብልጽግና አፍራሽ የፖለቲካ ባህልን በማረም ያለፈውን ታሪክ እያፈረሱ ከዜሮ የመጀመርን አድካሚና አክሳሪ ሂደት በማስቀረት፣ የነበሩ ጥንካሬዎችን የሚያስቀጥልና ድክመቶችን የሚያርም አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ ከፍቷል። ብልፅግና ሀገራችንን ለዘመናት ካቆረቆዛት የርዕዮተ-ዓለም ጥገኝነት በማላቀቅ፣ በተጨባጭ ውጤትና በብልጽግና ጉዞ ላይ ያተኮረ አመራር እየሰጠ ይገኛል፡፡
የብሔር ማንነት ሳይደፈቅና ብሔራዊ አንድነት ሳይላላ፣ ኢትዮጵያ በክብርና በታላቅነት እንድትቀጥል የሚያደርግ ብቸኛው አማራጭ ብልፅግና ነዉ፡፡
የለውጥ ጉዟችን እንዲቀጥል፣ ጠንካራና ተከባሪ ሀገር እንድንገነባ ምርጫችሁ ብልጽግና ፓርቲ ይሁን!
ምልክታችን፦ የስንዴ ነዶ ነዉ።
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌታዊት ሀገር!
#prosperity