በወራቤ ከተማ ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ አስመልክቶ የድጋፍ ሰልፍ ተካሔደ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በወራቤ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሔደ ነው ።
በድጋፍ ሰልፉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ፣የማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል የህዝብ ተወካዮች ዋና አፈ ጉባዔ ክብርት ፋጤ ሰርሞሎ፣ በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ( ዶ/ር ) ፣የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች፣ ክልል የስልጤ ዞን አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ተገኝተዋል።
"ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር "በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሔደ ባለው የድጋፍ ሰልፍ ያለፉት ስምንት የለውጥ አመታት ስኬቶችን የሚዘክሩና የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክቶች እየተስተጋቡ ይገኛል።
በድጋፍ ሰልፉ ምርጫዬ ብልጽግና ነው፣በዲጂታል ኢትዮጵያ ነገን መገንባት፣ጸጋን ወደ ሀብት፣ብልጽግናን እመርጣለሁ አሻራዬን አኖራለሁ፣ትላንትን ማከም ነገን መተለም እና ሌሎችም መፈክሮች ተስተጋብተዋል።
#prosperity